አትሌቲክስ ፣ እግር ኳስ እና ሌሎች ስፖርታዊ ክንዋኔዎች
ሰኞ፣ ኅዳር 3 2016
በዛሬው የስፖርት መሰናዶ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የተከናወኑ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ይዳሰሳሉ። የሔሪ ኬን እና ጊራሲ አስደናቂ ግብ የማግባት ችሎታ የታየበት የጀርመን ቡንደስሊጋ እንዲሁም አርሰናል ከፍተኛ መሻሻል የታየበት የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግን በተመለከተ ትንታኔ ይኖረናል ። ማንቸስተር ሲቲ ከቸልሲ ጋ ያደረጉት ጨዋታ በርካታ ግብ የተስተናገደበት እና የበርካቶችን ትኩረት የሳበ ነበር ። የአትሌቲክስ ስፖርት እና ብሔራዊ ቡድናችንን የተመለከቱ ሌሎች አጫጭር ዘገባዎችንም አካተናል ።
እግር ኳስ
የጥቅምት 27 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እንደጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር በ2026 በዩናይትድ ስቴት፤ ካናዳ እና ሜክሲኮ የጋራ ጥምረት በሚዘጋጀው የዓለም ዋንጫላይ ተሳታፊ ለመሆን የማጣሪያ ጨዋታውን ሴራሊዮን እና ከቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ ቡድኖች ጋ ኅዳር 5 እና 11 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በሞሮኮ ሜዳ ላይ ግጥሚያዎቹን እንደሚያከናውን ታውቋል ። የኢትዮጵያብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አዲሱ አሰልጣኝ በመሆንም ሰሞኑን መሾማቸው የተገለጠው ገብረመድኅን ኃይሌ የቡድናቸውን 23 ተጨዋቾች ስም ይፋ በማድረግ ቅድመ ዝግጅታቸውን በናዝሬት ወይንም አዳማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተሞች ሲያደርጉ መቆየታቸውም ታውቋል ።
አትሌቲክስ
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት ከመጨረሻዎቹ እጩ ተመራጮ መካከል አንዷ ሆና መመረን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ሰሞኑን ይፋ አድርጓል ። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ተቋም ባለፈው ወር ነበር ለአትሌቲክስ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ድረ ገጾች ለፍትኃዊ ጨዋነት የተሻለ አርዓያ የሆኑ ቅጽበታዊ ውድድሮች የታዩ የአትሌቶችን ድርጊቶች እንዲመርጡ ጥሪ አቅርቦ የነበረው ። በዚሁ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በተሰበሰቡ ድምፆች ሠረት የተመረጡ ሦስት አትሌቶችን በተመለከተ የዓለም አትሌቲክስ ሰሞኑን ይፋ አድርጓል ።
የጥቅምት 19 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባከነዚህም መካከል አንዷ ሆና የተመረጠችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት በዐሥር ሺህ ሜትር የሩጫ ፉክክር ዘርፍ 3ኛ ሆና ለሀገሯ የነሐስ ሜዳሊያ ባስመዘገበችበት በሐንጋሪ የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር ላይ የቅርብ ተፎካካሪዋ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሐሰን በመጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ መውደቋን ተከትሎ ለተሰንበት ውድድሯን ከፈጸመች በኋላ አትሌቷን ለማንሳት እና ለማበረታታት የወሰደችውን ርምጃ በፍትኃዊ ቅጨዋነት በእጩነት ለመመረጥ ምክንያት መሆኑም ታውቋል ። የአሸናፊዎች ማንነትም ይፋ የሚደረገው በመጪው ወር በሞናኮ በሚካሄደው የዓመቱ ምርች አትሌት ሽልማት ስነስርዓት ላይ መሆኑ ታውቋል ።
በአትሌቲክስየዓለማቀፉ አትሌቲክስ ማህበር በውድድር ወቅት መልካም ስነ ምግባር ላሳዩ አትሌቶች ለሚሰጠው ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ከመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ውስጥ መካተቷ ፤ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የተስተዋሉ ልብ አንጠልጣይ ውድድሮች እና የተመዘገቡ ውጤቶች ፤ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ፤ የፈረንሳይ ሊግ አንድ እና አውሮጳውያን ሃገራት ጀርመን ለምታስተናግደው ዩሮ 2024 የአውሮጳ ዋንጫ እያደረጉ ያለው ዝግጅት እና ሌሎችም ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ተዳሰዋል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ታምራት ዲንሳ