1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አትሌት ምስጋናው ዋቁማ በፓሪስ ኦሎምፒክ በእርምጃ ውድድር የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን አስመዘገበ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 25 2016

አትሌት ምስጋናው ውድድሩን የጨረሰው በ 1 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ሲሆን ውጤቱም በኢትዮጵያዉያን አትሌቶች የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተነግሯል። አትሌቱ የገባበት ሰዓት የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቦለታል።

Olympische Spiele 2024 - Äthiopischer Sportler Meseganaw Wakuma
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

አትሌት ምስጋናው ዋቁማ በፓሪስ ኦሎምፒክ በእርምጃ ውድድር የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን አስመዘገበ

This browser does not support the audio element.

በፓሪስ ኦሎምፒክዛሬ ጠዋት በተካሄደው የወንዶች የ20 ኪ/ሜ የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ምስጋናው ዋቁማ በስድሰተኝነት አጠናቋል። አትሌት ምስጋናው ውድድሩን የጨረሰው በ 1 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ሲሆን ውጤቱም በኢትዮጵያዉያን አትሌቶች የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተነግሯል። አትሌቱ የገባበት ሰዓት የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቦለታል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚካፈሉባቸው የፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች ደግሞ ነገ ምሽት ይካሄዳሉ። ከመካከላቸው  የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አንዱ ነው ። በውድድሩ የቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊው ሰለሞን ባረጋ ድሉን ለማስጠበቅ ይፋለማል ። አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሪሁ አረጋዊም በውድድሩ ተሳታፊ ናቸው ። አትሌት ቢኒያም መሀሪ ተጣባባቂ ነው። በሌሎች የማጣሪያ ውድድሮች ነገ ምሽት 1 ሰዓት ከ10 ላይ የሴቶች የ5 ሺ ሜትር ፣ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ የሴቶች የ800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ። በሴቶች 5 ሺህ ሜትር አ,ትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ፣ መዲና ኢሳ እና እጅጋየሁ ታዬ ይካፈላሉ ። በ800 ሜትር አትሌት ጽጌ ዱጉማ ፣ ሃብታም ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ ይገኛሉ ። 

ኂሩት መለሰ
ሃይማኖት ጥሩነህ 

አዜብ ታደሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW