1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በለንደን አቀባበል ተደረገላቸው

ሰኞ፣ ሰኔ 11 2010

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ብሪታኒያ ትናንት ማምሻውን አቀባበል ተደረገላቸው። አቶ አንዳርጋቸውን ለመቀበል በለንደን የተዘጋጀውን መርኃ-ግብር የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ ኣውጪ ግንባር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብዱረሕማን መሐዲን ጨምሮ የተቃውሞ ፖለቲከኞች፣ ደጋፊዎቻቸው እና በብሪታኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ታድመውበታል።  

UK Empfangszeremonie für Andargachew Tsige
ምስል DW/H. Demissie

(Beri London) Andargachw in London/MMT - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሥራቹ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በሚኖሩበት ብሪታኒያ ትናንት ማምሻውን አቀባበል ተደረገላቸው። አቶ አንዳርጋቸውን ለመቀበል በለንደን ከተማ በተዘጋጀው መርኃ-ግብር ላይ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ ኣውጪ ግንባር (ኦብነግ) የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብዱረሕማን መሐዲን ጨምሮ የተቃውሞ ፖለቲከኞች፣ ደጋፊዎቻቸው እና በብሪታኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ታድመውበታል።  አቶ አንዳርጋቸው በወቅቱ ባሰሙት ንግግር እንዲፈቱ ለወተወቱ ሁሉ ምሥጋቸውን አቅርበዋል።

አቶ አንዳርጋቸው ከእስር ከተፈቱ በኋላ አዲስ አበባ ላይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። በልዩ ሁኔታ ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር የተፈቱት አቶ አንዳርጋቸው ወደ ብሪታኒያ ከመጓዛቸው በፊት ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድን አግኘው ማነጋገራቸው አይዘነጋም። በለንደን ከተማ ትናንት ማምሻውን የተዘጋጀውን የአቀባበል መርኃ-ግብር የተከታተለችው ሐና ደምሴ የሚከተለውን ዘገባ ልካልናለች።

ሐና ደምሴ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW