1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግስት «ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ፣ ስልጣን መልቀቅ አለበት»: የሕግ ባለሙያ 

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ኅዳር 18 2010

በሳምንቱ መጨረሻ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሚኒስትር በቅርቡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ-ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ላይ የተከሰተዉ ግጭት ከኦሮሚያ 98፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ በኩል ደግሞ አምስት ተጠርጣርዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አሳውቀዋል።

Ähiopien Regierungssprecher Negeri Lencho
ምስል DW/Y. G. Egziabher

Oromia and Ethi-Somalia Unrest: Conflicting figure raises Concern - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ-ሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ላይ በተከሰተዉ ግጭት በሽዎች የሚቆጠሩ ከቄያቸዉ መፈናቀላቸዉ እና በመቶዎች ደግሞ ሕይወታቸዉን ማጣታቸዉን ስንዘግብ ቆይተናል። አሁንም ግጭቱ እንደቀጠለ ከአካባቢዉ የሚደርሰን መረጀ ያመለክታል። የፌደራል መንግሥት ችግሩን ለመፍታትና ተጠርጣርዎችን ወደ ፍትሕ ለማምጣት ችላ ብሏል በሚል የሚተቹ ብዙዎች ናቸዉ።

የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ነጋሪ ሌንጮ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በግጭቱ የተሳተፉ ግለሰቦችን መንግሥታቸዉ በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተጠቀሰዉ አካባቢ በተነሳዉ ግጭት የኢትዮጵያ-ሶማሌ ልዩ ፖሊስ መሳተፉ በተጎጂዎችም ሲነገር «የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትም የግጭቱ መንስኤ የድንበር ጉዳይ ሳይሆን የታጠቀ ኃይል ሰዉ እየገደለ እና አያፈናቅለ ይገኛል» እያለ ባለበት ወቅት እስካሁን ከሶማሌ ክልል አምስት ሰዎች ብቻ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ጥያቄ አስነስቷል። የሁለቱም ክልሎች አስተዳደር የኢሕአዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች በመሆነናቸዉ አንዱ ክልል ጥፋት ካጠፋ ኢሕአዴግ እንዳጠፋ ይቆጠራል ይላሉ የሕግ ባለሙያዉ አቶ ተማም አባቡልጉ።

በሺህዎች የሚቆጠር ሕዝብ በማፈናቀል እና ንብረት በማዉደም የተጠረጠሩት ሰዎች ከተጠቀሰዉ ቁጥር በላይ መሆናቸዉን የጠቆሙት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ተጠርጣሪዎችን ወደሕግ የማቅረቡ ሥራ የክልሎችም ኃላፊነት መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተዋል። የክልሎችን እና የማሕበረሰቡን ትብብር የሚጠይቀዉ ፌዴራል መንግሥቱ አቅም አጥቶ እንዳልሆ አቶ ተማም ይናገራሉ።

በዶይቼ ቬሌ ፌስቡክ ገፅ ላይ ጆቴ ጋማቹ በሚል ስም «ግጭቱን ያስነሣው አካል ማን እንደሆነ እየታወቀ ለምን ይህን የመሠለ ድራማ መስራት አስፈለገ? መንግስት ከጉዳዩ ነፃ ነው ለማስባል ነው?» በማለት  ጠይቀዋል። በዋትስፕ ቁጥር ላይ አስተያየት የላኩልን አንድ ግለሰብ ደግሞ «ግጭቱ በማንም ይነሳ በምንም፤ ግጭቱን ሲያባብሱና ህዝቡን ሲገድል የነበረዉ የሱማሌ ክልል ልዩ ኃይል ነበር። ይህ የማይካድ መራራ እውነታ ነው። ጥፋተኞቹን ለፍርድ ማቅረቡ ባልከፋ ግን ህዝብን ሲገድል የነበረ ኃይል ግን ዛሬም ለፍርድ ሲቀርብ እያየን አይደለም»። ሲሉ ሃሳባቸዉን ሰጥተዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW