1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አናሌና ቤርቦክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆኑ

ሰኞ፣ ግንቦት 25 2017

የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙ። ቤርቦክ በዚህ ቦታ ላይ ለመወዳደር የቀረቡ ብቸኛዋ እጩ መሆናቸው ታዉቋል።

ጀርመናዊትዋ አናሌና ቤርቦክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙ
ጀርመናዊትዋ አናሌና ቤርቦክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙምስል፦ Michael Kappeler/picture alliance/dpa

የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ዛሬ ተሾሙ። ቤርቦክ በዚህ ቦታ ላይ ለመወዳደር የቀረቡ ብቸኛዋ እጩ መሆናቸው ታዉቋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ቤርቦክ ቦታዉን ለመዉሰድ ባደረጉት የማመልከቻ ንግግር፣ «በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች ሀገራት ከሚታየዉ የማግለል ዝንባሌ አንፃር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ ነዉ» ሲሉ ተናግረዋል። 
የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒ ስትር አናሌና ቤርቦክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚደንትነት በምዕራብ አውሮጳ አገሮች እና በሌሎች የዓለም ሃገራት ይደገፋል። አዲሷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት አናሌና ቤርቦክ የስልጣን ዘመናቸው የሚጀምረው ከፊታችን መስከረም ወር ይሆናል። ስልጣኑም ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚዘልቅ ነዉ። 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW