1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አንድ ለአንድ፤ ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ጋር

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 4 2017

ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በደርግ ዘመነ መንግሥት ሥልጣን ላይ ከነበሩት ወገኖች አሁንም በሀገር ጉዳይ በግልፅ ሃሳብ አስተያየታቸውን ከሚሰነዝሩ መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።

Äthiopien Major Dawit Wolde Giorgis
ምስል፦ Privat

አንድ ለአንድ፤ ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ጋር

This browser does not support the audio element.

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከውትድርና አንስተው በዘመነ ደርግም በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ለዓመታት ኢትዮጵያን አገልግለዋል። የሐረር ጦር አካዳሚ ሁለተኛ ኮርስ ምሩቅ ናቸው።  በሀገር ውስጥና በውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ሕግን ተምረዋል አጥንተዋል። በደርግ ዘመነ ሥልጣን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን፤ እንዲሁም በዘመቻ መምሪያ በኃላፊነት አገልግለዋል።  ከሀገር ከተሰደዱ በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት በልዩ ልዩ መስኮች ሠርተዋል። አሁኑ ሙሉ ጊዜያቸውን የአፍሪቃ ስትራቴጂ እና የጸጥታ ጥናት ተቋምን በመምራት ምርምሮችን ያካሂዳሉ። ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ግለታሪካቸውን ጨምሮ የተለያዩ መጽሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል።

ቃለምልልሱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

  ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW