አንድ - ለአንድ፦ ከአቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ጋር
ዓርብ፣ ኅዳር 20 2017አንድ - ለአንድ፦ ከአቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ጋር
ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፎዋቸዉ የሚታወቁት አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ የዛሬዉ አንድ ለአንድ ዝግጅት እንግዳ ናቸዉ። ፖለቲከኛዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ በኢህአፓ፣ በኢህአዴግ እና በግንቦት ሰባት ውስጥ አስከ ትጥቅ ትግል ተሳትፈዋል። ዛሬ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከፖለቲካ መድረክ ጠፍተዋል ምን አጠፋቸዉ? ከፖለቲካዉ ዓለም ወጥተዋል ይሏቸዋል። እዉነት ይሆን? ጡረታ ወጡ እንዴ ? ጠይቀናቸዋል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየዉ ግጭት ጦርነት እና የፖለቲካ ቀዉስ ኢትዮጵያዉያን በራሳቸዉ በመነጋገር በራሳቸዉ በሚያመጡት መፍትሄ ቀዉሱን ሊያቆሙ የሚችሉበት እድል አለን ? መፍትሄ ሊያገኝበት የሚችል እድልስ አለ? ወይስ የዉጭ ጣልቃ ገብነት ወይም ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል? ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካነሳንላቸዉ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ነዉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ እና ለዉጥ መጣ ከተባለ ወዲህ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር መፈታታቸዉ ይታወቃል። ከእስር ከተፈቱ ወዲህ ብዙም ሳይቆዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ሰዉ ብሎም አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። እንደዉም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስት እርቅ እንዲወርድ ብሎም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የኤርትራዉን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲጨባበጡ፤ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ሰላም እንዲወርድ ያደረጉ ቁልፍ ግለሰብ እንደሆኑ ይነገራል።
ሙሉዉን ቃለ ምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!
አዜብ ታደሰ