1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አንድ ለአንድ፤ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ ግሩንበርግ

ዓርብ፣ ሰኔ 20 2017

ተወልዳ ያደገችው በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሀረር ከተማ ነው። ትምህርቷንም እዚያው ሀረር እና አዲስ አበባ ተማረች። ከዚያም ወደ ጋዜጠኝነቱ ዓለም ገባች። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለዓመታት ሠርታለች። ደራሲም ናት።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ ግሩንበርግ
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ ግሩንበርግ ምስል፦ Guenet Ayele Geruneberg/DW

አንድ ለአንድ

This browser does not support the audio element.

 

ብዙዎች የሚያውቋት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን በስደት ከሚገኙበት ሃራሬ ዚምባብዌ ድረስ ሄዳ በማነጋገር ስለእሳቸው ለንባብ ባበቃችው «የሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች» የተሰኙ ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት መጽሐፍት ነው። በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሐረር ከተማ ተወልዳ ያደገችው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ በኢትዮጵያ ቴሌቪዝን ለ10 ዓመታት በፕሮግራም አቅራቢነት አገልግላለች። ከዚያም ከደርግ ሥርዓት ውድቀት በኋላየበርካታ ጋዜጦች አሳታሚ የነበረች ሲሆን፤ በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚያተኩር የአንድ ወርሐዊ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሆናም ሠርታለች። ኑሮዋን በፈረንሳይ እና በኢትዮጵያ አድርጋለች። ኢትዮጵያንም ፈረንሳይንም እኩል ትወዳለች። ኢትዮጵያ የትውልድ ሀገሯ ናት። ፈረንሳይ የባለቤቷ እና የልጆቿ ሀገር።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ በቅርቡ ወደ ሃራሬ ተጉዛ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቤት መገኘቷን በማኅበራዊ መገናኛ ገጿ ባጋራችው መረጃ አሳውቃለች። የአሁኑ የሃራሬ ጉዞዋ ኮሎኔል መንግሥቱ በሥልጣን ዘመናው ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ጎልማሶች፤ እናትና አባቶች ማንበብና መጻፍ እንዲማሩ ዕድል ላመቻቸው የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ እውቅና የሰጠው « Ethiopian society partnership Advocacy» የተባለ ድርጅት ለእሳቸው ያዘጋጀውን ሽልማት ለመስጠት ነበር።

የኢትዮጵያ ፊደላትፎቶ ከማኅደርምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በወቅቱ የተቀረጸ አጭር ቪዲዮም በፌስቡክ ገጿ ከመረጃው ጋር አጋርታለች። የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ

«ማንበብና መጻፍ ዋናው ቁምነገር

 ከሕይወቴ ጎሎ ይቆጨኝ ጀመር» በሚለውና «አይኖሩም የማይጽፉ ጣቶች፤ አይኖሩም የማያነቡ ዐይኖች»ን በመሳሰሉ ቀስቃሽ ዝማሬዎች ታጅቦ እጅግ ሚሊየኖች ኢትዮጵያውስጥ ከከተማ እስከ ገጠር ከፊደል የተዋወቁበት ታሪካዊ ዘመቻ እንደነበር ይታወሳል። ዛሬ በርካቶች ከመሠረተ ትምህርት ተነስተው እስከ ከፍተኛ ትምህርት መዝለቅ መቻላቸው፤ እጅግ ብዙ እናትና አባቶች በጣት ከመፈረም ለመላቀቃቸው፤ የተለያዩ ጽሑፎችንም እራሳቸውን ችለው ለማንበብ ለመቻላቸው ባለውለታ ነው። በተደጋጋሚ ከቀድሞው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር ፊትለፊት ተገናኝታ ለመወያየት የቻለቸው  የአንድ ለአንድ እንግዳ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ ግሩንበርግ ስለጻፈችው የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች ምን ትላለች?

ቃለመጠይቁን ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ

ሸዋዬ ለገሠ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW