አንድ - ለ - አንድ፤ከአንጋፋ የሕግ ባለሙያና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ አመሐ መኮንን ጋር
ዓርብ፣ ሰኔ 27 2017
ማስታወቂያ
«በከባድ ነገሮች ተፈትኖ ማለፍን እመርጣለሁ» የሚሉት የሕግ ባለሙያና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ አመሐ መኮንን ይህን ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸው ደግሞ የሕግ ሙያ መሆኑን በማስላት በ1985 ዓ.ም የሕግ ትምህርታቸውን ተከታትለው ተመርቋል። በ1986 ዓ.ም የደርግ መንግስት ባለስልጣናትን በሰብአዊ መብት ለመክሰስ በተቋቋመው የልዩ አቃቤ ሕግ ፅሕፈት ቤት ለ 6 ወራት ያሕል በጀማሪ ባለሙያነት አገለገሉ። ከ1986 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ በፍትሕ ሚኒስቴር ከእጩ አቃቤ ሕግ እስከ ምክትል ረዳት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በተለያዩ ደረጃዎች አገልግሏል። ከፍትሕ ሚኒስቴር ስራዎቻቸው ጎን ለጎን በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አስተማሪ ሆነውም ሰርተዋል። ከ1999 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም በጥብቅና ሙያ ካገለገሉ በኋላ በዚሁ ዓመት ባቋቋኑት የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች የተባለ ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
አቶ አመሐ መኮንን ከሰፊው ልምዳቸው የተወሰኑትን እንዲያካፍሉን እንግዳ አድርገናቸዋል። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ያዳምጡ። ለባለእንጀራዎም ያጋሩ።
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ነጋሽ መሐመድ