አንድ ለ አንድ ፦ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፈደሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር
ዓርብ፣ ግንቦት 1 2017
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ዘንድሮም በኑሮ ውድነትና በሌሎችም የመብት መጓደሎች እንደሚሰቃዩ የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፈደሬሽን( ኢሠማኮ)አስታውቋል። አንድ ሚሊዮን አሥር ሺህ የተደራጁ አባላት ያሉት የኮንፈደሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በዓለም የሠራተኞች ቀን ሜይ ዴይ ዋዜማ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ሠራተኞች አንገብጋቢ ለሚሏቸው ጥያቄዎች ከመንግስት መልስ ባለማግኘታቸው ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል ብለዋል። በዚህም ምክንያት ዘንድሮ እለቱ የተከበረው «መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በቂ መልስ ይስጠን» በሚል መሪ ቃል ነበር ። መንግሥት የደመወዝ ቦርድ የሚያቋቁመውን ደንብ እንዲያወጣ ኢሠማኮ ጠየቀ
ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ዋና ዋና ችግሮች መካከል አሳሳቢው የሠራተኞች የኑሮ ሁኔታ፣ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል አለመወሰን የገቢ ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ አለመሆን እንደሚገኙበት የሠራተኞች ማኅበራት መሪዎች የአባሎቻቸው የመብት ጥያቄ እንዲከበር ሲጠይቁ ከስራ መባረር ፣ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ማድረግም ይጠቀሳሉ ብለዋል።የኢትዮጵያ ሠ/ማኅበራት ኮንፈደሬሽን 50ኛ ዓመት
አቶ ካሳሁን እንዳሉት የኮንፈደሬሽናቸው አባላት በ2015 ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማቅረብ ቢፈልጉም ተከልክለው ነበር። ሆኖም ከዚያ በኋላ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የመነጋገር እድል አግኝተው ችግሮቹ ለሚመለከታቸው አካላት ተላልፈውልናል ብለዋል። ይሁንና የተወሰኑት ጥያቄዎች መልስ ቢያገኙም ወሳኞቹ ጥያቄዎች ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ መልስ አላገኙም ሲሉም ተናግረዋል። ኮንፌደሬሽናቸው አሁንም እንደገና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመነጋገር ጥያቄ አቅርቧል።
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ