1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አንድ - ለ - አንድ:- የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሠላም ጥሪ

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017

የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከያዝነዉ ወር ማብቂያ ጀምሮ በአዲስ አበባና በሌሎች አምስት ክልልሎች የሰላም ጉባኤዎች ለማድረግ እየተዘጋጀ ነዉ።አዘጋጆቹ እንዳሉት ጉባኤዎቹ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ግጭቶች፣ጥቃትና ሥርዓተ አልበኝነት እንዲያበቃ የሚረዱ ሐሳቦች የሚጠቁሙበትና ለሁሉም ወገን የሠላም ጥሪ የሚደረግባቸዉ ናቸዉ

አቶ አሕመድ ሁሴን  የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት።«የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አባላት የሞቱ፣የታገቱ---አሉ»
አቶ አሕመድ ሁሴን፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት።አቶ አሕመድ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ በድሕነቱ እንኳን በሰላም እንዲኖር ጦርነትና ግጭት ሊያበቃ ይገባል።ምስል፦ Ethiopian Civil society organizations council

አንድ ለ አንድ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሠላም ጉባኤዎችና ጥሪ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከያዝነዉ ወር ማብቂያ ጀምሮ በአዲስ አበባና በሌሎች አምስት ክልልሎች የሰላም ጉባኤዎች ለማድረግ እየተዘጋጀ ነዉ።አዘጋጆቹ እንዳሉት ጉባኤዎቹ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ግጭቶች፣ጥቃትና ሥርዓተ አልበኝነት እንዲያበቃ የሚረዱ ሐሳቦች የሚጠቁሙበትና ለሁሉም ወገን የሠላም ጥሪ የሚደረግባቸዉ ናቸዉ።የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጉባኤዎቹን ለመጥራት የተዘጋጀዉ የኢትዮጵያ መንግስት የሲቪል ማሕበራትን የሚመለከተዉን ደንብ ለማሻሻል ረቂቅ አዋጅ በሚያዘጋጅበት ወቅት ነዉ።ረቂቁ  ያሳደረዉ ተፅዕኖ፣ የሰላም ጉባኤዉና ጥሪዉ የዛሬዉ የአንድ ለአንድ ቃለ መጠየቅ ርዕሶች ናቸዉ።ነጋሽ መሐመድ የምክር ቤቱን ፕሬዝደንት አቶ አሕመድ ሁሴንን አነጋግሯል።

አቶ አሕመድ በሲቪል ማሕረሰብ ድርጅት ሥራና አመሠራረት ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።እሳቸዉ 6/21 እያሉ የሚጠሩት ሕግ ወይም ደንብ በሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ላይ ያሰደረዉን «ተፅዕኖ» ያሉትን ጫና በጋራ ለመቋቋም ድርጅቶቹን በጋራ መድረክና መረብ ለማሰባሰብ በተደረገዉ ጥረትም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል።ጥረቱ ሠመረ።የሲቪል ማሕበራቱ ከጋራ መረብና መድረክ አልፈዉ ምክር ቤት መሠረቱ።አቶ አሕመድም የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝደንት፣በቅርቡ ደግሞ ፕሬዝደንት ሆኑ።

በዚሕ ቃለ መጠይቅ አቶ አሕመድ ካሉት ጥቂቱ----

«የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ፓርላማ (ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) አይደለም።ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤዉ ወይም ለአባል ድርጅቶች ነዉ»

«---የማሻሻያዉ ረቂቅ አዋጁ ሊያካትታቸዉ የሚገቡ ምክር ሐሳቦችን ወይም ኢምፑት እንዲሰጡን (ህብረቶችን) ጠይቀን ወደ 10---11 የሚሆኑ ሕብረቶች ለኛ ልከዋል።እኛም ያንን ኮንሶሊዴት አድርገን ለፍትሕ ሚንስቴርና ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስገብተናል።---»

 

«የሰላም ጥሪና ጉባኤ ለማድረግ አልዘገየንም።በተለያየ መንገድ የሰላም ጥሪ ስናደርግ ነበረ።አክቲቭ  የግጭት አካባቢዎችም ላይ  የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ዉይይት እንዲያደርጉ----የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋሉ።ዋጋም እየከፈሉ።»

 «የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አባል የሆኑ የሞቱ አሉ፣ የታገቱ አሉ፣አብረዉ የሚራቡ፣ የሚጠሙ አሉ።---» 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW