አንጋፋዋ ጋዜጠኛ ኢሌኒ መኩሪያ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 14 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት እድገት ታሪክ ቀዳሚ ከነበሩት አንጋፋ ጋዜጠኞች አንዷ እሌኒ መኩሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። የኢትዮጵያ ቴሌቪዝን በ1957 ዓ,ም ሲመሠረት የመጀመሪያ አንባቢ መሆኗ የሚነገርላት ጋዜጠኛ እሌኒ ለኢትዮጵያ ራዲዮ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለረዥም ዓመታት አገልግላለች። ጋዜጠኛ እሌኒ የኢትዮጵያ ሴት የመገናኛ ብዙሃን ማሕበርን ከመሠረቱና ካጠናከሩ አባላትም አንዷ በመሆን ትታወሳለች። ባደረባት ህመም ምክንያት ለረዥም ጊዜያት በሀገር ውስጥ እና በውጭም ህክምና ስትከታተል የቆየችው ታዋቂዋ ጋዜጠኛ ኢሌኒ መኩሪያ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም መለየቷን ሰምተናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ