አክራ፥ የኢትዮጵያ እቃ ጫኝ አውሮፕላን አደጋ
ቅዳሜ፣ ጥር 2 2007ማስታወቂያ
መነሻውን ከቶጎ ዋና ከተማ ሎሜ ያደረገው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ 05 ደቂቃ ለማረፍ ባደረገው ሙከራ ነው ችግር እንደገጠመው የተገለጠው። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሦስት ሠራተኞች ህክምና ተደርጎላቸው ከሐኪም ቤት መውጣታቸውን የዜና ምንጩ አክሎ ገልጿል። የጋና የበረራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት፤ የአደጋውን መንስኤ ማጣራት ጀምሯል። አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ወቅት የአየሩ ኹናቴ ንፋሣማ እና እይታን የሚጋርድ እንደነበረም አንዳንድ ዘገባዎች ጠቅሰዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ