1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አወዛጋቢው የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቡራኬ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 20 2016

የሮማ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በዓለም ዙሪያ እያወዛገበ ነው።በተለይ በአፍሪካ የካቶሊክ አማኞች ዘንድ የጳጳሱ ቡራኬ ተቃውሞ ገጥሞታል። ።

የሮማ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን  በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በዓለም ዙሪያ በተለይም በአፍሪካ እያወዛገበ ነው
የሮማ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን  በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በዓለም ዙሪያ በተለይም በአፍሪካ እያወዛገበ ነውምስል፦ GUGLIELMO MANGIAPANE/REUTERS

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ቡራኬ በአፍሪቃ ቁጣ ቀስቅሷል

This browser does not support the audio element.

 

የሮማ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን  በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በዓለም ዙሪያ በተለይም በአፍሪካ እያወዛገበ ነው።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በቅርቡ በፅሁፍ ባሰራጨችው ዘለግ ያለ መግለጫ«የቡራኬ ሀዋሪያዊ ትርጓሜ» በተሰኘው ሰነድ ምዕመኖቿ ብዥታ ውስጥ መግባታቸውን ገልፃ፤ በዚህ ሰነድ ላይ መወያየቷን እና ከዚህ በፊት በነበረው የጋብቻ አስተምህሮ  እና ቀኖና ላይ የፀና እምነት እንዳለት አስታውቃለች።

ቤተክርስቲያኒቱ አያይዛም ፤ጋብቻ በአንዲት ሴት እና በአንድ ወንድ ይፈፀማል በሚለው ቀኖና ላይ ምንም አይነት ለውጥ አለማድረጓን ገልፃለች።

እንደ ቤተክርስቲያኗ መግለጫ ሰነዱ ለተመሳሳይ ጾታ ጥምረት ዕውቅና ስለመስጠት እና በሚስጥረ ተክሊል ደረጃ ባል እና ሚስት አድርጎ ስለመባረክ ፈቃድ የመስጠት ሀሳብ  የለውም። በመሆኑም «ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በምንም አይነት አትፈቅድም።አታፀድቅምም»ስትል በመግለጫዋ አመልክታለች።

የሮማ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን  በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በዓለም ዙሪያ በተለይም በአፍሪካ እያወዛገበ ነውምስል፦ Tiziana Fabi/AFP/Getty Images

በሌላዋ አፍሪቃዊት ሀገር ናይጄሪያም አንዳንድ የካቶሊክ ምዕመናን ከቅዱስነታቸው  አዲስ መመሪያ ጋር ራሳቸውን ለማስታረቅ ተቸግረዋል።ዳቦህ የተባሉ የቤተክርስቲያኒቱ አባል፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ አነጋገር ሊጸና የማይችል ነው ይላሉ።

«መግለጫው የእሱ አስተያየት ሊሆን ይችላል። አምናለሁ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ እንኳን ተቀባይነት የለውም። በዚህ ጉዳይ ላይ በአሁኑ ጊዜ፣ ተቀባይነት ያለው ነገር ነው ብዬም አላምንም፣ እና በአጠቃላይ ተቀባይነት የለውም።».ሲሉ ተናግረዋል።

የናይጄሪያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳሱን እንደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ እና የእምነት ጠባቂ አድርገው ያከብራሉ።ሆኖም፣ ቤተ ክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጥንዶችን ትባርካለች የሚለው ሐሳብ በምእመናን አእምሮ ውስጥ ጥርጣሬ እንዲፈጠር አድርጓል።

የሮማ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታን ጋብቻን  በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በአፍሪካ እያወዛገበ ነውምስል፦ Vatican Media/AFP

ዶናተስ የተባሉ ሌላው ናይጄሪያዊ ምዕመን የጳጳሱን ሀሳብ የተረዱበትን መንገድ እንዲህ ይገልፃሉ።  

 «ጳጳሱ የግብረ ሰዶማውያንን ጋብቻ ስለመባረክ ሲናገሩ፤ እንደ እኔ ግንዛቤ ጋብቻው በሚስጥረ ተክሊል የተቀደሰ ሆኖ መባረክ አለበት ማለታቸው አይደለም።ያ አይሆንም»በማለት ገልፀዋል።

ሌላው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ማቲስ ሳቲ የጳጳሱን ዕይታ መቃወም እንደሚቻል ይጠቁማሉ።

«ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ የሚሉትን ሁሉ መከተል አለብን ማለት አይደለም። ቢያንስ እሳቸው እንዲያውቁት  ለመከራከር ቦታ ሊኖር ይገባል። ነገርግን እኛ አፍሪካውያን በእርግጠኝነት ይህ ባህላችን አይደለም። ለምንድነው ስህተት የሚሰራን ሰው የምትመርቀው? ለምን? እኔ ያዚያ ደጋፊ አይደለሁም።»ብለዋል።

የናይጄሪያ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፅ/ቤት በበኩሉ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ  የእግዚአብሔርን ሕግና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የሚጻረር ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ፀሀይ ጫኔ
ሂሩት መለሠ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW