1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢው የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 4 2017

ለዶቸ ቬሌ አስተያየታቸዉን የሰጡ የደሴ ከተማ ኗሪዎች እንደተናገሩት "የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ ገቢራዊ እንዲሆን በቻልነዉ መጠን አስተዋፅኦ ብናደርግም የተሰበሰበዉ ገንዘብ የት እንደደረሰ ሳናዉቅ ፕሮጀክቱ ቆሟል" ይላሉ።

Äthiopien Wello 2024 | Gebäude der Wello-Universität
ምስል Wello University Public relations department

አነጋጋሪው የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ

This browser does not support the audio element.

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ወጭ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ አሰባብ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉበት አስታወቀ።

የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ በ2003  አመተ ምህረት በኢትዮጵያ ያለዉን ህክምና ለማዘመን መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ሀብት የማሰባሰብ ሂደቱ የተጀመረ ቢሆንም ባለፋት 14 ዓመታት ግንባታዉን ለመከወን የተቋቋመዊ ኮሚቴ ምንም አይነት ግንባታ ሳይከዉን ቆይቷል ነው የተባለው።

እንደ ፌደራል ኦዲት ቢሮ ሪፖርት ከሆነ በተለያዮ ምክንያቶች ለግንባታዉ ከተሸጡ ኩፖንና ሎተሪዎች ገቢ መሆን የሚገባዉ ገንዘብ በክልሎች፣ ኢምባሲዎችና ግለሰቦች ገቢ አልተደረገም። 

የህዝብ አመኔታ ያጣው የሆስፒታሉ ግንባታ

ለዶቸ ቬሌ አስተያየታቸዉን የሰጡ የደሴ ከተማ ኗሪዎች እንደተናገሩት "የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ ገቢራዊ እንዲሆን በቻልነዉ መጠን አስተዋፅኦ ብናደርግም የተሰበሰበዉ ገንዘብ የት እንደደረሰ ሳናዉቅ ፕሮጀክቱ ቆሟል" ይላሉ።

ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ  በለዉጡ  ማግስት ከደሴ ከተማ ማህበረሰብ ጋር በነበራቸዉ ዉይይትም "ከህብተረተሰብ የተሰበሰበዉ ብር  ለአስተዋፅኦ የሚሆን ግንባታ ይሰራበት መንግስት በሪፈራል ሆስፒታል ደረጃ በራሱ ወጭ ግንባታዉን ይከዉናል" ብለዉ ነበር

ይሁን እንጂ ይህ ፕሮጀክቱን እንዲተገብር የተቋቋመዉ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እዉቅና ሳይኖረዉ ስራ እየከወነ ሲሆን የሆስፒታል ግንባታዉም ከኮሚቴዉ ወደ ወሎ ዮንቨርስቲ ተሸጋግሯል።

የወሎ ዩኒቨርስቲ ሕንጻዎች በከፊልምስል Wello University Public relations department

ገንዘቡን ለማስመለስ አቅም የለንም

ባክኗል ስለተባለዉ ገንዘብም የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ,ኃላፊ የሆኑት አቶ እሽቱ አየለ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሰብሰብ እንዳልቻሉ ይናገራሉ የአሜሪካና ሪያድ ኢምባሲዎች በግዜዉ የተሰጣቸዉን የገቢ ማሰባሰቢያ ኩፖን ወደገንዘብ ያልቀየሩ ሲሆን የአማራ ክልልን ጨምሮ በኦሮምያ ደቡብና  አፋር ከኩፖንና ሎተሪ ሽያጭ መገኘት የሚገባዉ ብር ገቢ አልተደረገም።

ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ ከ2010 ዓመተ ምህረት በኃላ  ህጋዊ ሆኖ መንቀሳቀስ ስለማይችል የሰበሰበዉን ገንዘብ ለማስረከብ ተረካቢ ማጣቱን ይይገልፃል።

አሁን የሆስፒታሉ ግንባታ በወሎ ዩንቭርስቲ እየተከወነ ነው

የወሎ ዮንቨርስቲ ፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት መልአክ እንደገለፁት ዩንቨርስቲዉ ለወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ ተብሎ የተመደበ በጀት ባይኖርም ስራዉን ለማጠናቀቅ እየሰራን ነዉ ይላሉ። ነገር ግን ከዚህ ቀደም ከህዝብ የተሰበሰበን ገንዘብ በተመለከተ አስፈላጊዉ ህጋዊ ኦዲት ሲከወን ተጠያቂነት ባለዉ መልኩ እንረከባለን ይላሉ።

የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ 3 ቢልየን ብር ይፈጃል ተብሎ ቢጀመርም እስካሁን የዋናዉ ሆስፒታል ግንባታ አልተጀመረም።
ኢሳያስ ገላው
አዜብ ታደሰ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW