አዉሮጳ በብራስልስ ሽብር ማግሥት
ረቡዕ፣ መጋቢት 14 2008ማስታወቂያ
ትናንት ብብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያ እና በአንድ የምድር ዉስጥ ባቡር ጣቢያ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ ሰላሳ-አንድ ሰዎች ተገድለዋል። ከ250 በላይ ቆስለዋል ። ቦምቡን ካፈነዱት መካከል ሁለቱ በፍንዳታዉ ሲሞቱ ሰወስተኛዉ አሁንም እንደተሰወረ ነዉ። የአዉሮጳ ከተሞች በተደጋጋሚ በአሸባሪዎች መጠቃታቸዉ ዳግም የመነጋገሪያ ርዕሥ ሆኗል።
የቤልጅግዋ ርዕሰ-ከተማ ብራስልስ ትናንት በአሸባሪዎች ከተጠቃኝ ወዲሕ እዚያዉ ቤልጂግ እና በአጎራባቾችዋ ሐገራት የሚደረገዉ የፀጥታ ጥበቃ እና ቁጥጥር ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። ከፍተኛ ቁጥጥር ከሚደረግባቸዉ ሐገራት አንዷ ጀርመን ናት። የጀርመን ፀጥታ አስከባሪዎች በተለይ ሐገሪቱን ከቤልጂግ፤ ከፈረንሳይ፤ ከኔዘርላንድስ እና ሉክስምቡርግ ጋር የሚያዋስኑ ድንበሮችን በጥብቅ እየፈተቆጣጠሩ ነዉ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደታዘበዉ ደግሞ አዉሮፕላን ማረፊያዎች፤ባቡር ጣቢያዎች፤ ሕዝብ የሚያዘወትራቸዉ የገበያ ማዕከላትም ባይነ ቁራኛ እየተጠበቁ ነዉ።
ገበያዉ ንጉሴ
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ