አዉሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ በሠልፍ አወገዙ
ረቡዕ፣ ኅዳር 17 2018
ማስታወቂያ
ጀርመን ዉስጥና በአጎራባች የአዉሮጳ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ፣ ግፍና ማፈናቀልን ዛሬ በርሊን-ጀርመን ዉስጥ ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍ አወገዙ። በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በጠራዉ ሰልፍ ላይ የታደሙት ሠልፈኞች እንደሚሉትየኢትዮጵያ መንግሥትበተለያዩ አካባባቢዎች «በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ» የሚፈፀመዉን ግድያና ግፍ እስካሁን ማስቆም አልቻለም።ግድያ፣ ግፍ፣ በደሉ እንዲቆም ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳርፍ ጠይቀዋልም። ነጋሽ መሐመድ ከሰልፉ አስተባባሪዎች ፣ ሊቀካሕናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን መስራችንና መላከ መዊ ልሳነ ወርቅ ዉቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመን ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መላከ መዊ ልሳነ ወርቅ ዉቤን በሥልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ