1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አውሮጶችን ያስቆጣው አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የደኅንነት ስልት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 30 2018

አውሮጳን በእጅጉ የሚተቸው በቅርቡ ይፋ የተደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የደኅንነት ስልት በእንግሊዘኛው ምህጻር NSS ሰነድ እያነጋገረ ነው። ሩስያን ደግፎ አውሮጳን የሚያጣጥለውን ይህን ሰንድ አውሮፓውያን እየኮነኑት ነው።

USA 2025 | Donald Trump veröffentlicht neue Nationale Sicherheitsstrategie
ምስል፦ Jean Pierre Nguyen Van Hai Barbier/ABACA/picture alliance

አውሮጶችን ያስቆጣው አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የደኅንነት ስልት

This browser does not support the audio element.

ዩናይትድ ስቴትስባለፈው አርብ ይፋ ያደረገችው አዲሱ ብሔራዊ የደኅንነት ስልት በተለይ አውሮጳ ላይ ያተኮረው የሰነዱ ክፍል አውሮጳውያን አጋሮችን ደካማ አድርጎ አቅርቧል። ሰነዱ ለቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞች ድብቅ ድጋፍ የሰጠና በአውሮጳ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትንና የክፍለ ዓለሙን የፍልሰት ፖሊሲ በጥብቅ የተቸም ነው። ይህም የአውሮጳ ኅብረትንና አባል ሀገራትን አስቆጥቷል። የኅብረቱ አባል ሀገራት የመሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶንዮ ኮስታ ዩናይትድ ስቴትስ በአውሮጳውያን ጉዳዮች ጣልቃ መግባቷን ተቃውመው፣ የአውሮጳ ዜጎችም  የትኛዎቹ ፓርቲዎች ሊመሯቸው እንደሚፈልጉ የሚወስኑት እነርሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። የአውሮጳ ኅብረት ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆኑ የጀርመንና የሌሎች የኅብረቱ አባል ሀገራት መሪዎችም በተለይ አውሮጳ ላይ  ባተኮረው የሰነዱ ክፍል ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

በሰነዱ ስለአውሮጳ የሰፈረውን የተለየ አገለጻጽ በመቃወም፣ ቅሬታቸውን ካቀረቡት መካከል ጀርመን አንዷ ናት ።የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሀን ቫደፉል የየዩናይትድ ስቴትስ የደኅንነት ስልት ሰነድን እንደሚገመግሙና ጉዳዩን ከሚያውቁ ባለሞያዎች ጋርም እንደሚመክሩበት አስታውቀዋል። ዩናይትድ ስቴትስም ዋነኛዋ አስፈላጊ አጋር ሆና እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። ሆኖም በሰነዱ ውስጥ ከተጠቀሰው የማይስማሙባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ሳይጠቅሱ አላለፉም ። 

«በጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ውስጥ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ጥያቁዎች ወይም እዚህ ጀርመን የነጻው ኅብረተሰባችን አደረጃጀት ጉዳይ የዚህ አካል በመሆናቸው አላምንም። ወይም ማንም በዚህ ጉዳይ ላይ ምክር ሊሰጠን ይገባል ብለን አናምን። ነገር ግን ይህ በሕገ መንግሥታዊ ሥርዓታችን የተደራጀ ነው ብለን እናምናለን።

ለዚህ ዓላማ ደግሞ የሦስቱ የመንግሥት ሥልጣን የአስፈጻሚው፣ የሕግ አውጪው እና የፍትህ አካላት ብቻ ሳይሆን  ነፃ ሚዲያም ጭምር አለ። እዚህ ላይ ለዚህ አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ እንሰጣለን ። እናም የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ እስካሁን ድረስ እነዚህን ጉዳዮች በውስጥ ሲወያይባቸው ቆይቷል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ወደፊት በራሳችን መወያየት እና መወያየት እንደምንችል እናምናለን ። እናም እና ምንም አይነት የውጭ ምክር አያስፈልገንም።»

የአውሮጳ ኅብረት የመሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶንዮ ኮስታ ምስል፦ Luisa Gonzalez/REUTERS

የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስም ተመሳሳይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። ሜርስ በሰጡት አስተያየት ጉዳዩ አዲስ እንዳይደለ ወደ ኋላ መለስ ብለው አስታውሰዋል። 
«ባለፈው ሳምንት ያነበብነው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት (ጄዲ ቫንስ) በየካቲት ወር በሙኒኩ የፀጥታ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት ጋር ይመሳሰላል። ከሰነዱ የተወሰነው ክፍል መረዳት ይቻላል ። ሆኖም አንዳንዶቹ ከኛ ከአውሮጳውያን እይታ አንጻር ተቀባይነት የላቸውም። አሜሪካውያን በአውሮጳ አሁን ዴሞክራሲን ለመዳን መፈለጋቸው እኔ እንደማየው አስፈላጊ አይደለም። መዳን ቢያስፈልገው ሮኖ ያንን እኛው ብቻችንን እናደርገዋለን።» 

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሀን ቫደፉል ምስል፦ Pedro Pardo/AFP/Getty Images

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የደኅንነት ስልት ከቀደሙት መሰል ሰነዶች የተለየ መሆኑንየብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ገልጿል። አውሮጶችን ያስቆጣው የአሜሪካን አዲሱ የደኅንነት ስልት አውሮጳች የደኅንነታችን ስጋት የሚሏትን ሩስያን አስደስቷል። ሩስያ ሰነዱን በደስታ ተቀብላለች ። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሰነዱን ከሩስያ ራዕይ ጋር አብሮ የሚሄድ ሲሉ አወድሰውታል።  

“በአዲሱ ፅንሰ-ሀሳብ ውስጥ የምናያቸው ልዩነቶች በእርግጥም ለኛ ማራኪ ይመስላሉ። የውይይት ገንቢ እና ወዳጃዊ ግንኙነቶችን የመገንባት አስፈላጊነትን ይጠቅሳል። ይህ እኛን ከመማረክ ውጪ ሌላ ሊሆን አይችልም፣ እና ከራዕያችን ጋር ሙሉ በሙሉ ይጣጣማል። በአሁኑ ጊዜ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ውስጥ ያሉትን የሚጎረብጡ (የሚያበሳጩ) ጉዳዮችን በማስወገድ፣ ግንኙነታችንን በእውነት ወደነበረበት ለመመለስ እና ከከባድ ቀውስ ለማውጣት የሚያስችል ተስፋ ሊከፍትልን እንደሚችል እንረዳለን።”

የጀርመን መራኄ መንግስት ፍሪድሪሽ ሜርስ ምስል፦ Lisi Niesner/REUTERS

ዋይት ሀውስ ይፋ ያደረገው ሰነድ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከሞስኮ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እንደምትፈልግ ያመለክታል። ሰነዱ ለአውሮጳ ምን ማለት እንደሆነ የተጠየቁት ሜርስ  መፍትሔው ከጥገኝነት ተላቆ ራሽን መቻል መሆኑን ተናግረዋል።

"ይህ ለደህንነት ፖሊሲ ትብብራችን ምን ማለት እንደሆነ የቀረበው ጥያቄ ፣በእርግጥ በጣም አስፈላጊው ጥያቄ ነው። ይህ በአውሮፓም ሆነ በጀርመን በደህንነት ፖሊሲ ረገድ ከአሜሪካ ይበልጥ ነፃ መሆን እንዳለብን ያለኝን ግምገማ ያረጋግጣል። ይህ አያስደንቅም።  ነገር ግን አሁን እንደገና ተረጋግጧል። ይህ የአሜሪካውያን አዲሱ ስልት ነው እና በእርግጥ 'አሜሪካ ፈርስት' ቅድሚያ ለአሜሪካ በተለይ እዚያ በተለይ ጠንከር ብሎ ተገልጿል። "

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW