አዲሱ የሶርያ የሰላም ድርድር በዠኔቭ6 መጋቢት 2008ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2008የሶርያ ተቀናቃኝ ወገኖች አምስት ዓመት የሆነውን የሀገራቸው የርስበርስ ጦርነት ለማብቃት የሚቻልበትን መፍትሔ ለማፈላልግ ከትናንት ጀምሮ በዠኔቭ ስዊትዘርላንድ እንደገና በመካሄድ ላይ ባለው አዲስ የሰላም ድርድር ተሳትፏቸውን እንደቀጠሉ ነው።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግየተመድ ልዩ የሶርያ ልዑክ ስታፈን ደ ሚስቱራምስል Reuters/R. Sprichማስታወቂያ በተመድ ልዩ የሶርያ ልዑክ ስታፈን ደ ሚስቱራ መሪነት የሚካሄደው ዤኔቭ ሶስት የተባለው ድርድር በሶርያ የሽግግር መንግሥት ስለሚቋቋምበት፣ አዲስ ሕገ መንግሥት ስለሚረቀቅበት፣ እንዲሁም ፣ በቀጣዮቹ 18 ወራት ውስጥ ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫዎች ስለሚደረጉበት ጉዳዮች ይመክራል። ገበያው ንጉሤ አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ