1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የአዉሮጳ ኮሚሽን የስደተኞች ፖሊሲ  

ሐሙስ፣ መስከረም 14 2013

የአዉሮጳ ኮሚሽን የኅብረቱን የስደተኞች እና የፈላስያን ፖሊሲ ረቂቅ ትናንት ይፋ አድርጎዋል። ኅብረቱ እስካሁን የጋራ እና ወጥ የስደተኞች ፖሊሲ እንዳልነበረዉ ይታወቃል። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም ተከስቶ ከነበረዉ የስደተኞች ቀዉስ ወዲህ ግን  የጋራ የስደተኞች ፖሊሲ ለማዘጋጀት ሞክሮ እስካሁን ሳይሳካለት ቆይቶአል።

Belgien Brüssel | Pressekonferenz Migrationspakt | EU-Kommission
ምስል Dursun Aydemir/picture-alliance/dpa

ኮሚሽኑ የጋራ የስደተኞች ፖሊሲ ለማዘጋጀት ሞክሮ እስካሁን ሳይሳካለት ቆይቶአል

This browser does not support the audio element.

የአዉሮጳ ኮሚሽን የኅብረቱን የስደተኞች እና የፈላስያን ፖሊሲ ረቂቅ ትናንት ይፋ አድርጎዋል። ኅብረቱ እስካሁን የጋራ እና ወጥ የስደተኞች ፖሊሲ እንዳልነበረዉ ይታወቃል። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም ተከስቶ ከነበረዉ የስደተኞች ቀዉስ ወዲህ ግን  የጋራ የስደተኞች ፖሊሲ ለማዘጋጀት ሞክሮ እስካሁን ሳይሳካለት ቆይቶአል። ዋናዉ የልዩነት ምክንያትም ስደተኞች በገፍ በሚገቡባቸዉ እንደግሪክ እና ጣልያን በመሳሰሉ ደቡባዊ የኅብረቱ ሃገሮች ያለዉን ጫና ሌሎቹ የኅብረቱ አባል መንግሥታት እንዲጋሩ እና  በስደተኞች አቀባበል እና አያያዝ  ላይም ተመሳሳይ አያያዝ እንዲኖር የሚጠይቀዉ የኮሚሽኑ እቅድ ነበር። ሁሉም የኅብረቱ ሃገሮች የሚያከብሩት እና የሚከተሉት የጋራ የስደተኞች ፖሊሲ አለመኖር፤ የአዉሮጳ ኅብረት አይነተኛ ድክመት ሆኖ ቆይቶአል።  

 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW