1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር

ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009

ግንባታው 3.4 ቢሊዮን ዶላር የፈጀው ይኽው የባቡር መስመር ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ሲጀምር በቀን 5,600 ሰዎች እና 3500 ቶን ቁሳቁሶችን ማመላለስ ይችላል

Äthiopien Einweihung von neuer Bahnstrecke
ምስል DW/G.T. Haile-Giorgis

Ber. A.A (Bahnstrecke Addis - Djibouti eingeweiht) - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

አዲስ አበባን ከጅቡቲ የሚያገናኘው አዲሱ የባቡር መስመር ዛሬ ተመረቀ ። በቻይና ኩባንያዎች የተሰራው ይኽው የባቡር መስመር ለኢትዮጵያ ልማት ብዙ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የኢትዮጵያ የባቡር መንገድ ኮርፖሬሽን ባለሥልጣናት ዛሬ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል ። 656 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ይኽው የባቡር መስመር ስራ ሲጀምር ቀድሞ ሦስት ቀናት ይፈጅ የነበረውን ጉዞ ወደ 12 እና 15 ሰዓት ዝቅ እንደሚያደርገው ተነግሯል ። ግንባታው 3.4 ቢሊዮን ዶላር የፈጀው ይኽው የባቡር መስመር ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ሲጀምር በቀን 5,600 ሰዎች እና 3500 ቶን ቁሳቁሶችን ማመላለስ ይችላል ተብሏል ። በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተገኝቷል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW