1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የካንሰር ህክምና ማዕከል በሀረር

ማክሰኞ፣ የካቲት 22 2014

ከቀናት በፊት በሀረር ህይወት ፋና ሆስፒታል የተሟላ የካንሰር ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ተደራጅቶ ክፍት የሆነው የህክምና ማዕከል በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እንግልት እና ድካም የሚያስቀር ትልቅ ተግባር መሆኑን ተገልጋዮች ገለፁ።

Äthiopien | Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital
ምስል Messay Teklu/DW

ከቀናት በፊት በሀረር ህይወት ፋና ሆስፒታል የተሟላ የካንሰር ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ተደራጅቶ ክፍት የሆነው የህክምና ማዕከል በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እንግልት እና ድካም የሚያስቀር ትልቅ ተግባር መሆኑን ተገልጋዮች ገለፁ። የጤና ሚንስቴር በሀገሪቱ ለአመታት አንድ ብቻ ሆኖ የዘለቀውን የካንሰር ህክምና ማዕከል ሰባት ለማድረስ እየሰራሁ ነው ብሏል። በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እና በጤና ሚንስትር የተቀናጀ ጥረት ሀረር በሚገኘው ህይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል ለአገልግሎት ክፍት በሆነው የካንሰር ህክምና ማዕከል ቤተሰብ በማሳከም ቀዳሚ ተገልጋይ እንደሆኑ ለDW የገለፁ የድሬደዋ ነዋሪ አገልግሎቱ በቅርብ መጀመሩ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል። 

በማዕከሉ እየተገለገሉ ካሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ነዋሪዎች መካከል ሁለቱ ባገኙት ህክምና የጤናቸው ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑን የሆኑ አስተያየት ሰጭዎች ተከታዩን ብለዋል። የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለረዥም አመታት በሀገሪቱ አንድ ብቻ በነበረው የካንሰር ህክምና ማዕከል አገልግሎት ለማግኘት ከነበረው እንግልት ባለፈ የሰዎች ህይወት ጭምር ያልፍ እንደነበር ጠቅሰው በአሁን ሰዓት ተመሳሳይ ማዕከላትን ወደ ሰባት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኡርጌ ዩኒቨርሲቲው ምርምር በማካሄድ የማዕከሉን አገልግሎት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል። ከቀናት በፊት በሀረር ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የካንሰር ህክምና ማዕከል ከሁለት መቶ ሰባ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተገልፆል።

መሳይ ተክሉ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW