1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኤኮኖሚሰሜን አሜሪካ

አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ ቀረጥ እና የተቀረው ዓለም ምላሽ

ሐሙስ፣ መጋቢት 25 2017

ፕረዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትላንትናው ተመጣጣኝ ያሉትን ከፍተኛ የሆነ ቀረጥ በበርካታ የአለም ሃገራት ላይ ጥለዋል። ይሄው ወደሃገር ውስጥ በሚገቡ እቃወች ላይ የተጣለው ቀረጥ ዋና ግቡ የተዛባውን የውጪ ንግድ ለማስተካከል እንደሆነ ቢነገርም፣ ለአሜሪካውያን የዋጋ ንረትንና የእኢኮኖሚን ማሽቆቆልን ሊያመጣ እንድሚችል ተጠቁሟል።

USA, Washington | US-Präsident Donald Trump
ምስል፦ Mark Schiefelbein/AP/dpa/picture alliance

ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የጣሉት ቀረጥ ምን ይዞ መጣ?

This browser does not support the audio element.

ፕረዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትላንትናው ተመጣጣኝ ያሉትን  ከፍተኛ የሆነ ቀረጥ በበርካታ የአለም ሃገራት ላይ ጥለዋል። ይሄው ወደሃገር ውስጥ በሚገቡ እቃወች ላይ የተጣለው ቀረጥ ዋና ግቡ የተዛባውን የውጪ ንግድ ለማስተካከል እንደሆነ ቢነገርም፣ ለአሜሪካውያን የዋጋ ንረትንና የእኢኮኖሚን ማሽቆቆልን ሊያመጣ እንድሚችል ተጠቁሟል። የዚሁ የትራምፕ አዲስ የገቢ ቀረጥ ኢላማ የሆኑ ሃገራትም ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል።

ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የትላንትናውን እለት “የአሜሪካ የኢኮኖሚ ነጻነት ቀን” ብለው ነው የሰየሙት ። እናም የፕሬዝዳንታዊ የአደጋ ጊዜ ስልጣንን ተጠቅመው የንግድ ጦርነት እንደማወጅ የተቆጠረውን፣ ከፍተኛ የሆነ የገቢ ቀረጥ በ185 ሃገራት ላይ ጥለዋል።

የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ

ፕሬዝዳንቱ 34 በመቶ አዲስ ቀረጥ የተጣለባትን ቻይናን እና 20 በመቶ የተጣለባቸውን የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ጨምሮ፣ ከአሜሪካ ጋ ከፍተኛ የንግድ ግንኙነት ባላቸውና በከፍተኛ ሁኔታ ያልተመታጠነ የውጪ ንግድ እጥረት ውስጥ በሚገኙ 60 በሚሆኑ ሃገራት ላይ ከፍተኛ ቀረጥን ጥለዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎች ሃገራት በሚመጡ ሸቀጣሸቀጦች ላይ ደግሞ ዝቅተኛ መነሻ የተባለውን አስር በመቶ የቀረጥ ግዴታን ጥለዋል።

የአሜሪካ አጋር ሃገራትን ጨምሮ በርካታ የአለም ሃገራት ለዚሁ የትራምፕ የቀረጥ ጫና  ተመሳሳይ የመልስ እርምጃ እንደሚሰጡ ዝተዋል።  ዓለም አቀፉ የንግድ ምክር ቤትም የንግድ ውጥረቱ እየተባባሰ መሄዱ "ለዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት ግልጽ የሆነ አደጋ" እንዳሚሆን ገልጿል።

ቻይና ጃፓን እና እና ኮሪያ ለዶናልድ ትራምፕ ቀረጥ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋልምስል፦ Colourbox

የትራምፕ ውሳኔና ዳፋው

እያንዳንዳቸው ከ20በመቶ በላይ የቀረጥ ግዴታ የተጣለባቸው ቻይና፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ለዚሁ ውሳኔ በጋራ ምላሽ እንድሚሰጡ አስታውቀዋል።  

የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሺንባውም ደግሞ ለዚሁ የቀረጥ ሳኔ ምላሽ የሚሆን ሰፊ የኤኮኖሚ እቅድ ይፋ እንደሚደረጉ ተናግረዋል።

የተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት መሪዎችም ይሄው አዲስ የቀረጥ ጫና በየሃገሮቻቸው ላይ የሚኖረውን ትርጉም ገምግመው ተመጣጣኝ ምላሽ እንድሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ አዲሶች የትራሞፕ ውሳኔወች "በዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት ላይ መሠረታዊ ለውጥ እንደሚያመጡ ገልጸው፣ አስፈላጊውን የመከላከያ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።

የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ፓሪስ ውስጥ ሊገናኙ ነው

የሚሰማቸው ያገኙ ባይመስልም የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት የአለም ሃገራት የአጸፋ ምላሽ ከመስጠት እንዲቆጠብይ አሳስበዋል።

የአውሮጳ ህብረት ለዶናልድ ትራምፕ የቀረጥ ዉሳኔ የአጸፋ እርምጃ መልስ ይሰጣሉ ምስል፦ Daniel Kalker/picture alliance

የገቢ ቀረጡ ጫናና እሰጣገባው ማቆምያ ወደሌለው የንግድ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችልና በአሜሪካ ገበያ ውስጥ የዋጋ ንረትና በአሜሪካ ሸማቾች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫናን ከመፍጠር የተለየ ጠቀሜታ እንደማይኖረው ተፈርቷል።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትርና፣ የኢኮኖሚ መማክርት ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉት ፣ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፈሠሩ ላሪ ሰመር ይሄንኑ የትራምፕ የቀረጥ ጫና በአሜሪካና በአሚሪካውያን ላይ በሁሉም መንገድ ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ ሲሉ ገልጸውታል።

አበበ ፈለቀ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW