1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ ጀርመን የስደተኞች ሕግ

ሰኞ፣ ሐምሌ 4 2014

የጀርመን ጥምር መንግስት በአገሪቱ ላለፉት 5 ዓመታት የቆዩት ስደተኞች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙበትን ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በተለይ ጉዳያቸው በእንጥልል ለነበረ ኢትዮጵያውያንና አፍሪቃውያን እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW ተናግረዋል።

Spanien Hunderte Flüchtlinge stürmen in spanische Nordafrika-Enklave
ምስል imago/Agencia EFE/Reduan

አዲሱ የጀርመን የስደተኞች ሕግ

This browser does not support the audio element.

የጀርመን ጥምር መንግስት በአገሪቱ ላለፉት 5 ዓመታት የቆዩት ስደተኞች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙበትን ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በተለይ ጉዳያቸው በእንጥልል ለነበረ ኢትዮጵያውያንና አፍሪቃውያን እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW ተናግረዋል።  
ጀርመን ሀገር በተለያየ ምክንያት ገብተው በስደት የሚኖሩ ከ242ሺ በላይ የብዙ አገራት ዜጎች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። ከነዚህ  ላለፉት 5 ዓመታትና ከዛም በላይ በጀርመን ጊዜያዊ ፈቃድ አግኝተው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ ከነበሩት መካከል ወደ 136 ሺ የሚሆኑት ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲፈጠር የጀርመን ጥምር መንግስት ውሳኔ አሳልፏል። የሕግና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና ባለሙያ ዶክተር ለማ ይፍራሽዋ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተውናል። እንደሳቸው ገለጻ ጥር ወር 2022 በፊት በጀርመን ከ5 ዓመታት በላይ የቆዩ, ምንምዓይነት የወንጀል መዝገብ የሌላቸው ስደየኞች ለሁሉም የሙከራ ጊዜ የአንድ አመት im,ኖሪያ ፈቃድ ከተሰጠ ቦኋላ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት መብትን ያጎናጽፋቸዋል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ሕጉ ለጀርመኖች ኢኮኖሚና ለአፍሪቃውያን በተለይ ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች እፎይታን የሚሰጥ ነው ብሎታል። በአዲሱ ሕግ መሰረት በሞያ የሰለጠኑ ተቀጣሪዎች ወደፊት ቤተሰቦቻቸውን ወደ ጀርመን ሲያስመጡ ተጥሎ የነበረው የጀርመንኛ ቋንቋ የማወቅ ቅድመ ግዴታ አሁን ተነስቷል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW