1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አመት: የአይጥ ዘመን በቻይና

ሰኞ፣ የካቲት 10 2000

የሶስተኛዉን አምዐት በተቀበልንበት አመት ህዝባዊት ቻይናም በያዝነዉ ወር በራስዋን የቀን ቀመር መሰረት አዲስ አመትን ተቀብላለች። በቻይና አዲስ አመት በስራ በትምህርት ምክንያት ከቤተሰብ ከወላዳጅ ዘመድ የተራራቀ ሁሉ የሚገናኝበት በድምቀት የሚከበር ተወዳጅ በአል ነዉ

አዲስ አመት አከባበር በቻይና
አዲስ አመት አከባበር በቻይናምስል AP

በዘንድሮዉ የቻይና አዲስ አመት በተለይ በደቡባዊትዋ የአገሪቷ ክልል የጣለዉ በረዶ የየብሱንም ሆነ የአየሩን የትራንስፖርት መገናኛ ለሳምንታት አደንዝዞት መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም ምክንያት ከዘመድ ወዳጅ ለመገናኘት አዲስ አመትን በጋራ ለማክበር የቸኮሉ በርካታ ቻይናዉያን በአየር እና በባቡር ጣብያ አዲሱን አመትን የተቀበሉ ጥቂት አይደሉም። ቻይናዉያን በባህላዊ የቀን ቀመራቸዉ ስንተኛ አመት ደረሱ ላላችሁ፣ ቻይናዉያን የኣሳማዉን ዘመን አጠናቀዉ እነሆ ወደ አይጥ ዘመን ተሸጋግረዋል!
ዘንድሮ በአይጥ ዘመን ቻይናዉያን መልካም ነገር እንደሚመጣ ያምናሉ፣ ምክንያቱን የአይጥ ዘመን ለቻይናዉያን በጎ ነገር የሚከሰትበት፣ ሃብት፣ ሰላም የሚበዛበት በመሆኑ! በዚህም ምክንያት ይላሉ ያገሪዉ ጠበብቶች በያዝነዉ አመት በቻይና በርካታ ህጻናት ይወለዳሉ። ስለቻይናዉያን ባህላዊ የቀን ቀመር ያጠናቀርነዉን ያድምጡ መልካም ቆይታ!

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW