1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባ በአዲስ ዓመት የበዓል ዋዜማ

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 5 2014

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ለወትሮው ዘመን መቀየሩን አዲስ አመት መምጣቱን በሚያበስሩት አደይ አበባ ባያሽበርቁም ፣ የመስቀል ወፍ ዝር ባይልባቸውም አልፎ አልፎ በዓሉን በዓል ለማድረግ ዘመን መለወጡን ለመብሰር ያህል በቢጫ እና ነጭ ፕላስቲክ ፊኛዎች ደምቀዋል።

Äthiopien I Mädchen singen 'Abebayehosh' zur Feier von Enkutatash, dem äthiopischen Neujahrsfest Addis Abeba
ምስል Author Hana Demissie/DW

የአዲስ አበባ የአዲስ ዓመት የበዓል ዋዜማ

This browser does not support the audio element.

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ለወትሮው ዘመን መቀየሩን አዲስ አመት መምጣቱን በሚያበስሩት አደይ አበባ ባያሽበርቁም  ፣ የመስቀል ወፍ ዝር ባይልባቸውም  አልፎ አልፎ በዓሉን በዓል ለማድረግ ዘመን መለወጡን ለመብሰር ያህል በቢጫ እና ነጭ ፕላስቲክ ፊኛዎች ደምቀዋል። የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ባንኮች እና ምግብ ቤቶች ትንሹም ትልቁም ቄጤማ ጎዝጉዘው የበዓል ሙዚቃ ከፍተው ቡና ከነረከቦቱ አቅርበው በሞንታርቦ   የከተማውን ነዋሪ፣ አላፊ አግዳሚውን የአዲስ ዓመት አመት በዓል መሆኑን ይናገራሉ።

ምስል Author Hana Demissie/DW

ህብረተሰቡም እንቁጣጣሽህን ይነስም ይብዛ እንዳቅሙ ለማክበር በየገበያው ይተራመሳል፣ዋጋ ያማርጣል ፣ያውዳድራል። እኔም ገበያውን ምን ይመስል እደሆነ ለማየት የተለያዪ ጉልቶችን እና መካከለኛ እና ከዛ በላይ የኑሮ ደረጃ ያለቸው ሰዎች ይገበይዪበታል የትባሉትን ትልልቅ ሱፕር  ማርኬቶች ተዘዋውሬ ቃኝቻለሁ

 ‘ዘመኑ ከፍቶዋል ልጂ ተውድዋል እሳት ነው ይፋጃል መቺስ እርሱ ፈቅዶ ዘመን ካሻገረን ይመስገን ነው ‘ያሉኝ እናት  ዘንድሮ ዘይቱን በቅቤዋጋ ስለገዛሁት ቅቤ አልገዛሁም ይላሉ

የሚጎዘጎዘው ቂጠማ በፊት 10 ብር የነበረው አሁን 20 ብር ነው  ልጆች ተሰብስበው በየመንደሩ የሚያበሩት ችቦ ቅጥነቱን ጭራሮ ቢባል ማጋነን አይሆንም የሚጠየቅበት ዋጋ ይከብደዋል።

2015 የኢትዪጵያ አዲስ አመት ዋዚውማ የተለያዪ ሪዲዮን እና  ቲሌቪዥን በትእዛዝ ይመስል እየተቀባበሉ የበአል ሙዚቃ ያለረፍት የሚያጫውቱት ሙዘቃ ለአፍታ የበአል ስሜት ቢፈጥርም የኑሮ ውድነት ጦርነቱ እና አለመረጋጋቱ  እያሽነፈው ደስታው እንዳይዘልቅ ድባቡ እንደወትሮው እንዳይደምቅ ሆኗል።

መጭው አመት ቸር የምናይበት ቸር የምንሰመበት አመት ይሁንልን መልካም አዲስ አመት ።

ሃና ደምሴ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW