1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሕግ እና ፍትሕኢትዮጵያ

አዲስ ዓመትን በይቅርታ በሲዳማ ክልል

ማክሰኞ፣ መስከረም 1 2016

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 205 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ ። ዶቼ ቬለ DW ዛሬ ጠዋት ከሀዋሳ ማረሚያ ቤት በይቅርታ ሲወጡ ያነጋገራቸው የይቅርታው ተጠቃሚዎች በአዲሱ ዓመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል መቻላቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል ፡፡

የቀድሞዎቹ እስረኞች በዘመን መለወጫ ዕለት  በመለቃቃቸዉ ከፍተኛ ደስታ እንደተማቸዉ አስታዉቀዋል።
የሲዳማ ክልል የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በይቅርት ከለቀቃቸዉ እስረኞች በከፊል።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ሲዳማ ክልል፦ ለ1,205 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

This browser does not support the audio element.

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 205 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ ። ዶቼ ቬለ DW ዛሬ ጠዋት ከሀዋሳ ማረሚያ ቤት በይቅርታ ሲወጡ ያነጋገራቸው የይቅርታው ተጠቃሚዎች በአዲሱ ዓመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል መቻላቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል ፡፡

ተራሚዎቹ በይቅርታ እንዲፈቱ የተደረገው አዲሱ ዓመት የምህረት ዓመት በመሆኑ ነው ያሉት የሲዳማ ክልል የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ «ታራሚዎቹ በይቅርታ ከመውጣታቸው በፊት በቀጣይ ሕግን አክብረው እንዲኖሩ  የሚያስችላቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል» ብለዋል፡፡

የምሕረቱ ተጠቃሚ የሆኑ ታራሚች 

ዛሬ ጠዋት የአዲሱ የ2016 ዓ ም የመጀመሪያ ቀን ጀምበር በማለዳ ደምቃ ወጥታለች ፡፡ ለወትሮው የቆዘሙ ፊቶች ጎልተው በሚታዩበት የሀዋሳ ማረሚያ ቤት ዛሬ ሌላ ገጽታን የተላበሰ ይመስላል ፡፡ የይቅርታ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸው የተገለጸላቸው ታራሚዎች ረጅም የደስታ ጭብጨባ ግቢውን አድምቆታል ፡፡

ከምሕረቱ ተጠቃሚ ታራሚች አንዱ የሆኑt አቶ ኮንታኖ ቡርቃምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ  ይቅርታ ካደረገላቸው ለ1 ሺህ 205 የሕግ ታራሚዎች መካከል 500 ያህሉ በሀዋሳ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ናቸው ፡፡ እነኝህ ታራሚዎች ይቅርታውን ያገኙት በክልሉ ህገመንግስት ለይቅርታ በሚፈቅደው አዋጅ መሠረት በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት ታይቶና ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቀርቦ ይሁንታን በማግኘቱ ነው ተብሏል፡፡

ሠልፍ በሀዋሳ

ከሀዋሳ ማረሚያ ቤት የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑ ታራሚዎች በፊታቸው የደስታ ድባብ ይስተዋልባቸዋል ፡፡ አብዛኞቹም ግቢውን ለቀው ለመውጣት የቸኮሉ ይመስላሉ ፡፡ አስተያየታቸውን ያጋሩኝ የይቅርታው ተጠቃሚዎች በአዲሱ ዓመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል በመቻላቸው መደሰታቸውን ነግረውኛል ፡፡

ከሀዋሳ ማረሚያ ቤት የምህረቱ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑ ታራሚዎች መካከል አንዷምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ታራሚዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊቀላቀሉ ነው

«አብዛኞቻችን ሲነገረን አላመንም ሁሉም ነገር የድንገት ነው የሆነብን» ያሉት ታራሚዎቹ  «በአዲሱ ዓመት ወደ ቤተሰቦቻችን በመቀላቀላችን ዕድለኞች ነን ፡፡ የማረሚያ ቤት ቆይታችን ከዚህ በኋላ ከወንጀል መራቅ እንዳለብን አስተምሮናል ፡፡ ሌሎችም ከእኛ ሊማሩ ይገባል» ብለዋል፡፡

ታራሚዎቹ በይቅርታ እንዲፈቱ የተደረገው የኢትዮጵያአዲሱ ዓመት የምህረት ዓመት በመሆኑ ነው ይላሉ  የሲዳማ ክልል የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ ፡፡ " ታራሚዎቹ በይቅርታ ከመውጣታቸው በፊት በቀጣይ ህግን አክብረው እንዲኖሩ የሚያስችላቸው ገለጻ መደረጉንም ኮሚሽነር ኮንታሞ ተናግረዋል ፡፡

ታራሚዎቹም በፈፀሙት ወንጀል በመፀፀት  የይቅርታ ማመልከቻ ማቅረባቸውን የተናገሩት ኮሚሽነሩ " ከማረሚያ ቤቶች ወጥተው ከህብረተሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ የበደሉትን ህዝብ ለመካስም ቃል ገብተዋል  " ብለዋል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW