አዲስ ዓመት በ ዲሲ እና አካባቢው
ረቡዕ፣ መስከረም 1 2017ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው ይሄው የዘመን መለወጫ በዓል በግ ማረድን ጨምሮ የአመት በዓል ግባዓቶች ግብይትንም ያካተተ ነው። እንቁጣጣሽ ከሃገር ቤት ርቆ ከመከበሩ ውጪ የተሟላ መሆኑን የገለጹት ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉም የአዲስ አመት ምኞታቸው በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ ማየት ነው።
የ2017 አዲስ አመት በአሜሪካ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየተከበረ ነው። በአሉ በጾምና በስራ ቀን በመዋሉ በአብዛኛው በአሉ የሚከበረው ከነገ ጀምሮ በተለይም ቅዳሜና እሁድ መሆኑ ተገልጿል። ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው ይሄው የዘመን መለወጫ በአል በግ ማረድን ጨምሮ የአመት በአል ግባዓቶች ግብይትንም ያካተተ ነው። በአሉ ከሃገር ቤት ርቆ ከመከበሩ ውጪ የተሟላ መሆኑን የገለጹት ያነጋገርናቸው እኢትዮጵያውያን ሁሉም የአዲስ አመት ምኞታቸው በእኢትዮያ ውስጥ ሰላምን ማየት ነው።
አዲሱ አመት ልክ እንደሃገርቤት በደመቀ ሁኔታ ነው የሚከበረው። በዋዜማው የተለያዩ የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች የአዲሱን አመት መምጣት በባህላዊ ምግቦችና የኪነጥበብ ድግስ አክብረዋል። በትላንትናው ምሽት ጎራ ብዬ ያየሁት አርሊንግተን ውስጥ የሚገኘው የሜዳ ኮፊ ኪችን ባለቤት አቶ ሲሳይ ድማሙ ምሽቱ የእኢትዮጵያን ትውፊት ባማከለ መልኩ እያከበሩ መሆኑን ገልጸውልኛል።
ዛሬ አዲሱ ዓመት እሮብ ላይ እንደመዋሉና እለቱም ስራ ያለበት እንደመሆኑ ሃበሻ በሚታይባቸው አካባቢወች ላይ የወትሮው ግርግር አይታይም። አሌክሳንድሪያ ውስጥ የሚገኘው የናዝሬት ባልትና ባልደረቦችም ለበአሉ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች አሟልተው ደምበኞቻቸውን ሲያስተናግዱ ነው ያገኘኋቸው።
አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ የአመት በዓሉ ገበያ እንዳለ ነው ብለዋል። በገበያ ማዕከሉ ስጋ ቤት ውስጥ ሲሰራ ያገኘሁት ፍሰሃ ታደሰም በዓሉ ከዋለበት ቀን ጋ ተያይዞ የስግአው ገበያ ደብዘዝ እንዳለ ጠቁሟል።
ከገበያ ሲወጡ ያገኘኋቸው ሜሊ በተለይ በዲሲ፣ ቨርጂኒያ እና ሜሪላንድ ውስጥ አመት በዓሉ ከእኢትዮጵያ ባልተናነሰ መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል። ዛሬ ቀለል ባለ ሁኔታ እያከበሩት እንደሆነና፣ የበለጠ ከቤተሰብ ጋ ያሚያከብሩት ከነገ ጀምሮ እንደሆነም ገልጸዋል። ሜሊና ቤተሰቦቻቸው እዚህ ሃገር እንደተለመደው ወደ ከብት አርቢ ገበሬወች ሄደው በግ አሳርደው መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
የናይስ ጸጉር ቤት ውስጥ በጸጉር አስተካካይነት ሲሰራ ያገኘሁት ወንድወሰን ብርሃኑ፣ የስራው ባህሪ አዲሱን አመት ጨምሮ አመት በዓሎችን ለማክበር እንደማይመች ነግሮኛል። አመት በዓሉን ከሃገር ርቆ ከማክበሩ በስተቀር የጎደለ ነገር የለም። የሁሉም እኢትዮጵያውያንና ትውልደ እኢትዮጵያውያን ልብ ኝ ሃገራቸው ላይ እንደቀረ የሁሉም የአዲስ አመት ምኞት አመላካች ሆኗል።
አበበ ፈለቀ
ልደት አበበ
ነጋሽ መሀመድ