1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ዓመት እና እቅዶች

ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2004

ብዙ ሰዎች አዲስ አመት ሲመጣ እቅድ ያወጣሉ። እናንተስ ለ2004 ካቀዳችሁት ምን ያህሉን ከግብ አደረሳችሁ? ምን ያህሉስ ሳይሳኩ ቀሩ? በዕቅድ መኖር ምን ትርጉም አለው?

Arbeitsmaterial Kundenservice #1505473 © Bobo Ling - Fotolia.com
እቅድ የሚፃፍበት የማስታወሻ ደብተር ላይ መፃፍ በጀርመን የተለመደ ነው።ምስል Fotolia/B. Ling

ለዛሬ አራት ወጣቶችን መጪውን አመት 2005 ዓ ም አስመልክቶ አዲስ እቅድ በአዲስ አመት ያወጡ እንደው ጠይቀናቸዋል። ወጣት አዲሱ ግርማ ፤ ከ አዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ በአካባቢያዊ እና ክፍለ ሀገራዊ ፕሮግራም በዚህ አመት 2ኛ ዲግሪውን አግኝቷል። ያለ እቅድ እንደ ማይንቀሳቀስ ነው የነገረን።ለምን እንደሆነ ገልፆልናል።

እቅዶችምስል Fotolia/Mellimage

ህይወት ይልማ 20 ዓመቷ ነው። እቅድ እስካሁን ኖሮኝ አያውቅም ትላለች፤

ሌላው ወጣት አህመድ ማሕመድ ነው ከጅማ። በከተማ ጥናት ነው የተመረቀው። እሱም እንደ አዲሱ በእቅድ መኖር ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል።

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንስ በየትኛው የዘመን አቆጣጠር ነው እቅድ የሚያወጡት?ስንዱ ፀጋዬ በባድ ሆምቡርግ ከተማ ነው የምትኖረው፤ ጨርሶ እቅድ ሳወጣ ቅርብ ጊዜዬ ነው ብላናለች። የኢትዮጵያው አዲስ አመት እቅዷን ለማደስ ጥሩ አጋጣሚ የሆነላት ይመስላል።

ወጣቶቹ ለሰጡንን አስተያየት ማድመጥ ይቻላል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW