1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አድዋ እንዴት ይዘከር?

ሐሙስ፣ የካቲት 23 2015

አድዋ ሲዘከር የአጼ ምኒሊክ እና የጦር አበጋዞቻቸው ተክለ ስብዕና ዘመን ተሻግሮ ያወዛግባል። ከ127 ዓመታት በፊት ለነጻነታቸው ቀናዒ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የተገኘው ድል ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የተሳተፉበት ነው። ታዲያ የአድዋ ዝክር ለምን ያወዛግባል? ወደፊትስ እንዴት ይዘከር?

120. Jahrestag der Schlacht von Adwa
ምስል Yared Sumete

አድዋ እንዴት ይዘከር?

This browser does not support the audio element.

የአድዋ ድል 127ኛ ዓመት መታሰቢያ ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2015 በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት የተለያዩ ስሜቶች ተከብሯል። በመሀል አዲስ አበባ በሚገኘው የምኒሊክ ሐውልት አጠገብ በዓሉን ለማክበር የተሰበበሰቡ ታዳሚያንን የጸጥታ አስከባሪዎች በኃይል በትነዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀው ሁለተኛ ዝክር ከባድ የጦር መሣሪያዎች በሰልፍ የታዩበት ነው። ማለዳ ከምኒሊክ ሐውልት ሥር ጉንጉን አበባ ያኖሩት ርዕሠ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በመስቀል አደባባይ በነበረው መርሐ-ግብር ታድመዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዦች እና የክልል መንግሥታት ፕሬዝደንቶች የተገኙበት ሁለተኛው የአድዋ ዝክር በወታደራዊ ሰልፍ የታጀበ ነበር።

ሁለቱም መርሐ ግብሮች ለነጻነታቸው ቀናዒ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ባሕር ተሻግሮ፤ ድንበር አቋርጦ የመጣባቸውን የጣልያን ወራሪ ጦር ድል የነሱበትን 127ኛ ዓመት ለመዘከር የተዘጋጁ ናቸው። አድዋ ሲዘከር በታሪክ ስማቸው የሚነሳ የቀድሞ የአገሪቱ መሪዎች እና የጦር አበጋዞች ተክለ ስብዕናዎች የሚሰጣቸው ትኩረት የመወዛገቢያ ማዕከል ሆኖ ይታያል። ለመሆኑ አድዋ እንዴት ይዘከር? በዚህ መሰናዶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ንድፈ ሐሳብ፣ የመንግሥት እና ሕብረተሰብ ግንኙነት ተመራማሪው ዶክተር ዮናስ አሽኔ እና የታሪክ ተመራማሪው ዶክተር ኢብራሒም ሙሉሸዋ ሐሳባቸውን አጋርተዋል።

ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW