1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አገር በቀል የሲቪል ማኅበራት ለሰላም ጥሪ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ተከለከሉ

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2014

የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል «CARD» ጨምሮ 35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች «አስቸኳይ የሰላም ጥሪ» ያሉትን ጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ተከለከሉ። ተከለከሉ። ድርጅቶቹ ዛሬ ማክሰኞ ጷጉሜ 1 ቀን 2014 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫውን ሊሰጡ የነበረው በአዲስ አበባው ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ነበር።

Äthiopien Center for Advancement of Rights and Democracy | Aktion Urgent Call for Peace!
ምስል CARD

ድርጅቶቹ በማንና ለምን እንደተከለከሉ በዉል አልተነገራቸዉም

This browser does not support the audio element.

የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል «CARD» ጨምሮ 35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች «አስቸኳይ የሰላም ጥሪ» ያሉትን  ጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ተከለከሉ። ተከለከሉ። ድርጅቶቹ ዛሬ ማክሰኞ ጷጉሜ 1 ቀን  2014 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫውን ሊሰጡ የነበረው በአዲስ አበባው ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ነበር። ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ የነበሩት ድርጅቶች የተሰባሰቡት፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ስላሳሰባቸው መሆኑን ለመገናኛ ብዙኃን አስቀድመው በላኩት ደብዳቤ ገልጸው በጋዜጣዊ መግለጫዉ ላይ እንዲካፈሉ ጋብዘዉ ነበር። ይሁን እና ጋዜጠኞቹ ከየትኛዉ ቦታ እንደመጡ ባልታወቁ የመንግሥት ባለሥልጣናት መከልከላቸዉን የሲቪክ ማኅበራቱ ተናግረዋል።   የኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ሰራተኞችም አሁኑ ስብሰባ አይኖርም በማለት ለጋዜጠኞቹ ማስታወቃቸዉን አካባቢዉ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶቹ የተፈጸመባቸውን ክልከላ «የሕግ የበላይነትን የሚፃረርና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም ሊጫወቱ የሚገባቸውን ድርሻ የሚነፍግ ሲሉ በድረገጻቸው ባወጡት መግለጫ ኮንነውታል። የመብቶች እና ዶሞክራሲ እድገት ማዕከል «CARD» ዋና ዳይሬክተር አቶ በፈቃዱ ኃይሉን አነጋግረናል።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW