1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

“አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ” እና የእንክብካቤ ጥያቄ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 18 2016

የኢትዮጵያ መንግስት “አረንጓዴ አሻራ” ብሎ በሰየመው እና ለተከታታይ ዓመታት ሲያከናውን የነበረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ትናንት ዐርብ ከ615 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በዘመቻ መተከላቸውን አስታውቋል። በመራሃ ግብሩ በዘመቻ የሚተከለው ችግኝ ምን ያህሉ ጸደቀ የሚለው ጥያቄ ግን መልስ ያሻል።

የኢትዮጵያ መንግስት “አረንጓዴ አሻራ”  ብሎ በሰየመው እና ለተከታታይ ዓመታት ሲያከናውን የነበረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር
የኢትዮጵያ መንግስት “አረንጓዴ አሻራ” ብሎ በሰየመው እና ለተከታታይ ዓመታት ሲያከናውን የነበረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ትናንት ዐርብ ከ615 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በዘመቻ መተከላቸውን አስታውቋል። ምስል Seyoum Getu/DW

በዘመቻ የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይሆን?

This browser does not support the audio element.

“አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ” እና  የእንክብካቤ ጥያቄ

የኢትዮጵያ መንግስት “አረንጓዴ አሻራ”  ብሎ በሰየመው እና ለተከታታይ ዓመታት ሲያከናውን የነበረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ትናንት ዐርብ ከ615 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በዘመቻ መተከላቸውን አስታውቋል።

መርሃ ግብሩ ለዓመታት ባካሄዳቸው የችግኝ ተከላ   በብዙ ቢሊየን የሚቆጠር ችግኝ መተከሉን መንግስት በተደጋጋሚ ሲገልጽ     ቆይቷል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ለአካባቢ ጥበቃ የሚኖረው ጉልህ ሚና ጥያቄ ውስጥ ባይገባም በዘመቻ የሚተከለው ችግኝ ምን ያህሉ ጸደቀ የሚለው  ጥያቄ ግን መልስ ያሻል።

የአካባቢ ጥበቃ  ባለሙያዎች እንደሚሉት ለችግኝ ተከላው በተሰጠው ትኩረት ልክ እንክብካቤውም ትኩረት ሊያገኝ ይገባዋል ባይ ናቸው ።

«ነገን ዛሬ እንትከል» አረንጓዴ አሻራ

ትናንት ዓርብ ነሃሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. መንግስት በአንድ ጀንበር ማለትም በ12 ሰዓታት ውስጥ 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ከ615 ሚሊዮን ችግኞችን በላይ መትከል መቻሉን አሳውቋል፡፡ በጂኦስፓሻል መረጃ ተገኘ በተባለው በዚህ በአንድ ቀን የችግኝ ተከላው ተሳትፎ 29 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች በ 318.4 ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች መትከላቸውም ነው የተብራራው፡፡

ይህም ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ የትናንቱን ጨምሮ አርባ ቢሊየን ገደማ ችግኞችን መትከል መቻሉ ነው በመንግስት በኩል የሚገለጸው፡፡ በትናትናው እለት በቤቢሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ በችግኝ ተከላ ዘመቻው ላይ ተሳትፈው ባደረጉበት ወቅት ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢህ አህመድ በዘንድሮ ዓመት ከሚተከሉ ችግኞች ለመግብነትና ለተለያዩ ጥቅሞች የሚውሉ 50 በመቶውን ይሸፍናሉም ነበር ያሉት፡፡

በአንድ ቀን 500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ

“በዘንድሮ ዓመት ከምንተክለው ከ7 ቢሊየን በላይ ችግኞች ከ50 በመቶ በላዩ ለምግብነት፣ ለመድሃኒትነትና ለአፈር መሸርሸር መከላከል የሚውል ነው፡፡ ቀሪው ደግሞ ለውበትና አከባቢ ጥበቃ የሚውል ነው” ብለዋል፡፡

“በዘንድሮ ዓመት ከምንተክለው ከ7 ቢሊየን በላይ ችግኞች ከ50 በመቶ በላዩ ለምግብነት፣ ለመድሃኒትነትና ለአፈር መሸርሸር መከላከል የሚውል ነው፡፡ ቀሪው ደግሞ ለውበትና አከባቢ ጥበቃ የሚውል ነውምስል Seyoum Getu/DW

በኦሮሚያ ደን ልማት ውስጥ በደን ልማት ባለሙያነት የሚሰሩት አቶ ተስፋዬ ኦዳ ባለፉት ኣመታት በዘመቻ የተደረገው የችግን ተከላ መርሃግበሮቹ ካላቸው የደን ልማት ማሻሻያ ፋይዳቸው ባሻገር የህብረተሰቡን አመለካከት በመቀየርም አኳያ ጉልህ አሻራ ያኖረ ይሉታል፡፡ ለዚህም ማሳያ ያቀርባሉ፡፡ “በራስ ተነሳሽነት ዛፍ ለመትከልና ለመንከባከል መነሳሳቱ ሁኔታ ከፍ ብሏል፡፡ የሚተከሉት ዛፎችም በሺዎች ሄክታር የሚቆጠር የተራቆቱ ስፍራዎችን መልሶ በማልማት የተለያዩ የአከባቢ እና አፈር ጥበቃ ፋይዳዎች ይኖሩታል” ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላው የኅብረተሰቡ ተሳትፎ

መንግስት እያከናወነ ባለው በዘመቻ ዛፎችን የመትከል ተግባር ምንያህሉ የእንክብካቤ ክትትል ተደርጎላቸው ይጸድቃሉ የሚለው ጥያቄ ግን በበርካቶች የሚነሳ ነው፡፡ ባለሙያው አቶ ተስፋዬ ግን ለሚተከሉ ዛፎች በየአከባቢው ክትትል እንደሚደረግ ነው የሚያነሱት፡፡ “በየቦታው ለሚተከሉት የጸደቁት ይቆጠራሉ” የሚሉት ባለሙያው የመጽደቅ ምጣኔውም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ መምጣቱንና በተሌም እንክብካቤ በሚደረግባቸው አከባቢዎች ከ85 በመቶ ገደማ እንደሚጸድቁ አመልክተዋል፡፡

የቀጠለው ችግኝ ተከላና ተስፋው

በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በግብርናና አከባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በመምህርነትና በተመራማሪነት የሚያገለግሉት እንዲሁም በኮሌጁ ተባባሪ ዲን የሆኑት ረዳት ፕሮፈሰር ሰለሞን እስጥፋኖስ ግን በዚህ ቁጥር የሚስማሙ አይመስልም፡፡ በየዓመቱ በተደጋጋሚ ችግኝ የሚተከልባቸው ስፍራዎች መኖራቸውንም በአብነት አንስተው፤ ከሚተከሉት ችግኞች ከ80 በመቶ በላይ የጽድቀት መጠን ይኖራል የሚለውን ለሪፖርት ብቻ የሚደረግ እንዳይሆን ይሰጋሉ፡፡

ባለሞያዎች በየዓመቱ በተደጋጋሚ ችግኝ የሚተከልባቸው ስፍራዎች መኖራቸውንም በአብነት አንስተው፤ ከሚተከሉት ችግኞች ከ80 በመቶ በላይ የጽድቀት መጠን ይኖራል የሚለውን ለሪፖርት ብቻ የሚደረግ እንዳይሆን ይሰጋሉምስል Seyoum Getu/DW

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት

“ክልሎች ተከላን አከናውነው የጽድቀት መጠንን ሪፖርት ሲያደርጉ ውድድር የሚመስል ነገር ይስተዋላል፡፡ ከዚያ መውጣቱ አስፈላጊ መስሎ ይታየኛል፡፡ ምክንያቱም ክልሎች ባላቸው የአቅም መጠን የመትከል አቅማቸውም ይለያያል፡፡ እናም ምን ያህሉ ጸድቋል የሚለው አከራካሪ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይ ከ70-90 ሪፖርት የሚያደርጉ አሉ፡፡ ነገር ግን እንደ ባለሙያ ምልከታችን እሱን አያሳይመም፡፡ አንድ ቦታ ላይ ለተከታታይ አራት ዓመት መልሰን መላልሰን ችግኝ የተከልንባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ከሚተከል እንደው ግማሹ ከጸደቀ ጥሩ ነው ብያስብልም ይህን ያህል ጸድቋል ብሎ በቁጥር ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው” ብለዋል፡፡

ዛፎችን መትከል እና መጠቀም

ያም ሆኖ ግን መሰል ችግኝን በዘመቻ የመትከል ጥረቱ ከ45 በመቶ ወደ 3 በመቶ ብቻ የወረዳውን የኢትዮጵያን የደን ልማት ሽፋን ከማሻሻል አንጻር አስተዋጽ እንዳለው ባለሙያው አመልክተዋል፡፡ ከ2000 ዓ.ም. ወዲህ በተለያዩ መንገዶች በተደረጉ የችግኝ ተከላ ንቅናቄዎች ብሎም በተወሰዱ አከባቢዎችን ከልሎ የመጠበቅ እርምጃዎች የአገሪቱ የደን ሽፋን መጠን አወዛጋቢ ብሆንም ከ15-20 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችልም ባለሙያው አስገንዝበዋል፡፡

ሰል ችግኝን በዘመቻ የመትከል ጥረቱ ከ45 በመቶ ወደ 3 በመቶ ብቻ የወረዳውን የኢትዮጵያን የደን ልማት ሽፋን ከማሻሻል አንጻር አስተዋጽ እንዳለውምስል Seyoum Getu/DW

በዘመቻ የተተከሉ ችግኞችን መልሶ በመከታተል በሚተከል ልክ የመጽደቅ ምጣነው ከፍ እንዲል አስፈላጊው ክትትል እንደሚያስፈልግም ምክረ ሀሳብ ተሰጥቷል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW