አጭር ቃለምልልስ ከኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ጋር
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2017
በአምስት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ 14 ዓመታትን የፈጀው የግድቡ ግንባታ ፈተና የጀመረው፤ ከመጀመሪያው ጀምሮ በአንድ ኮንትራክተር ስሥራ ከነበረበት ወደ ሁለት ሲከፈል ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የግድቡ ሥራ አስከያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፤ ያ የግድቡ ግንባታ ላይ ጊዜ መፍጀቱን ጠቁመዋል፡፡
ከዚያን በመቀጠል በግንባታው ላይ ያጋጠሙ ትላልቅ አለቶችን የማውጣት ሥራ ሌላ ብርቱ ሥራ እና ጊዜን የወሰደ ነበር ያሉት ሥራ አስከያጁ፤ መነሻው ላይ የነበረው የሥራ ጥራትም ጉድለት የነበረበት በመሆኑ አፍርሶ መሥራት አስፈልጎ ነበር ብለዋል፡፡ "ፕሮጀክቱ ተስፋ የለውም እስከመባል ደርሶም ነበር” ያሉት ኢንጂነር ክፍሌ በፕሮጀክቶ ላይ በተሰራው የማሻሻያ ሥራ ግን "ፕሮጀክቱ ነፍስ በመዝራቱ” የተልእኮ ጦርነትን ጨምሮ በርካታ ፈተናዎች በሥራው ላይ መጋረጥ ጀምረዋልም ነው ያሉት፡፡
"እስከ 200ኪ.ሜ. ወታደሩ ፈንጂ በእግር እየተጓዘ በማምከን የፕሮጀክት ግብዓቶችን ማጓጓዝ ተችሏልም” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጡ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በርካታ ሰው ሰሠሽ ፈተናዎች ፕሮጀክቱን ስፈታተኑትም እንደነበር አስረድተዋል፡፡ ግብዓቶች እንዳይኖሩ የሲሚንቶ ፋብሪካን ለመምታም ተሞክሯል ሲሉ የችገግሩን ውስብስበነት ዘርዝረዋል፡፡ ግድቡ መሰል ውስብስብ ፈተናዎች የደረሱበትም ከታችኛው ተፋሰስ አገራት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ግድቡን በመገንባት ሂደት ውስጥ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል ያሉት ኢንጂነር ክፍሌ በሂደቱ ሕይወታቸውን ያጡትን በቁጥር ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል፡፡ "የተልኮ ጦርነት ነበር” ሲሉ የችግሩን ውስብስብነትም ሲያስረዱ "ተልእኮውን የተቀበሉም ሆኑ ችግሩን ለማምከን የሰሩ በርካታ ኢትዮጵያውን በግድቡ ግንባታ ሂደት ውስጥ ሕይወታቸውን ስለማጣታቸው” ግን አረገግጠዋል፡፡
ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የህዳሴ ግደቡን ግዝፈት ለመግለጽ በሰጡት ማብራሪያም፤ ግድቡ በኤሌክትሪክ ማምነጫት አቅሙ ከአፍሪቃ ቀዳሚ፤ እንዲሁም በያዘው የውኃ መጠን ወይም በሐይቁ ግዝፈት ደግሞ ከአጉሪቱ አራተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ውኃን የያዘው የግብጹ አስዋን ግድብ 132 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውኃን በመያዝ በአፍሪቃ ቀዳሚ ነው፡፡ ህዳሴ ግድብ 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውኃ በመያዝ ከአፍሪቃ አራተኛው ግዙፍ የሰው ሠራሽ ሐይቅ ነው፡፡ ሌሎች በአፍሪቃ ውስጥ የሚገኙ ግድቦች መስኖን ጨምሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲውሉ ህዳሴ ግድብ ግን በኤሌክትሪክ ማመንጨት ላይ ብቻ የሚሰራ መሆኑ በኤሌክትሪክ ማምንጨት ቀዳሚው የአፍሪቃ ግድብ ተሰኝቷል፡፡
"ወደ 10.7 ሚሊየን ሜትርኪዩብ ኮንክሪት በመውሰድ ህዳሴ ግድብ በዓለም ላይ ትልቁ ነው” ሲሉም የተከፈለበትን አምስት ቢሊየን ዶላር ግድም ወጪን ጨምሮ በከፍተኛ ደረጃ የተለፋበት ግድብ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ግድቡ ድንበር ተሸጋሪ ወንዝ ላይ የተገነባ ፕሮጀክት እንደመሆኑ በግንባታው ላይ የተሳተፉ ኮንትራክተሮች ዓለም ላይ የታወቁ ናቸው ያሉት ኢንጂነር ክፍሌ፤ የውጭ ኮንትራክተሮቹ ማሽነሪን የማቅረብና አንዳንድ ሥራዎችን ከመከወን ውጪ ከ90 በመቶ በላይ ግድቡ በአገር ውስጥ ባለሙያዎች አቅም እንዲሁም 100 በመቶ በአገር ውስጥ የፋይናንስ አቅም መሠራቱንም ጠቅሰው፤ ከፕሮጀክቱ ሥራ ትልቅ አገራዊ ልምድ መገኘቱንም አንስተዋል፡፡ ከፋይናንስም ባሻገር ፕሮጀክቱ አፍሪቃውያን በራሳቸው አቅም እና ሃብት እራሳቸውን ማልማት እንደሚችሉ ትምህርት የሰጠ ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
"በግድቡ ግንባታ ከ28 ሺህ - 30 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ሞያዎች ተሳትፈዋል” ያሉት ሥራ አስከያጁ፤ ይህ ፕሮጀክት ያሰረጠው የአንድነት መንፈስ በጉልኅ እንደሚጠቀስም አስገንዝበዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ