1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፈር ፣ ምርታማነት እና የማዳበሪያ አጠቃቀም

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 18 2015

ከክረምቱን የዝናብ እና የእርሻ ወቅት ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለኬሚካል የአፈር ማዳበሪያ እጥረት መነገር ከጀመረ ሰነባበተ። አርሶ አደሩ ኅብረተሰብ ከራሱ አልፎ መላውን ሕዝብ ለመመገብ የሚያስችል ምርት እንዲያገኝ ኬሚካል የአፈር ማዳበሪያን መጠቀም ለጊዜው አማራጭ እንደሌለው በአፈር ምርታማነት ምርምር ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

Afrika Bauer Symbolbild German food partnership
ምስል Imago

አፈር ፣ ምርታማነት እና የማዳበሪያ አጠቃቀም

This browser does not support the audio element.

በተለያዩ ምክንያቶች ለምነቱን የሚያጣ አፈር ምርታማ እንዲሆን ማዳበሪያ መጠቀም ከተጀመረ የመቶ ዓመታት ታሪክ እንዳስመዘገበ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከፍተኛ የሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ፣ ፀረ ተባይና በምርምር የተሻሻሉ ዘሮችን በሚጠቀሙ የምዕራቡ ዓለም ሃገራት ቢኖሩም በእነዚሁ ሃገራት በተፈጥሮ መንገድ የተመረቱ የእርሻ ውጤቶች ዋጋቸው ከፍተኛ ነው። የአፈርን ምርታማነትን ለማሻሻል የአፈር ማዳበሪያ ጠቃሚ ቢሆንም በጤናም ሆነ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያመላክቱ ጥናቶችም አሉ።  

ከክረምቱን የዝናብ እና የእርሻ ወቅት ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለኬሚካል የአፈር ማዳበሪያ እጥረት መነገር ከጀመረ ሰነባበተ። አርሶ አደሩ ኅብረተሰብ ከራሱ አልፎ መላውን ሕዝብ ለመመገብ የሚያስችል ምርት እንዲያገኝ ኬሚካል የአፈር ማዳበሪያን መጠቀም ለጊዜው አማራጭ እንደሌለው በአፈር ምርታማነት ምርምር ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ኬሚካል የአፈር ማዳበሪያ መጠቀም ምርት እና ምርታማነት እንደሚያሳድግ የሚገልጹ ወገኖች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አብዛኛው ሕዝባቸው በግብርናው ዘርፍ ለሚተዳደር ሆኖም በቂ ምርት ማምረት ለሚያቅተው ሀገር ብዙ አምርቶ ከረሀብ ለመዳን እንደዋና መፍትሄ አድርገው ያቀርባሉ። በአንጻሩ ለረዥም ጊዜያት የኬሚካል ማዳበሪያ መጠቀም በአፈሩ ላይ ዘላቂ እና ሊቀለበስ የሚያዳግት ችግር እንደሚያስከትል የተለያዩ ጥናቶች  ያመለክታሉ። ቀደም ብለው የኬሚካል አፈር ማዳበሪያ በአፈሩ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ዘላቂ ጉዳት አስቀድመው የተረዱ የአካባቢ ተፈጥሮ ደህንነት ተቆርቋሪዎች አርሶ አደሩ በአካባቢው ባለ ተረፈ ምርት አማካኝነት የተፈጥሮ ማዳበሪያ እንዲያዘጋጅ ቢወተውቱም የኬሚካል ማደበሪያው ሽያጭ ዘርፉ ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ ተግባራዊነቱ እንዳይበረታታ እንቅፋት ሆኗል በሚል የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎች ይሞግታሉ። ይኽም ውሎ አድሮ አርሶ አደሩ በኬሚካል ማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት መሬቱን እንደወትሮው አርሶ መዝራት እንዳልቻለ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ድምጹን ለማሰማት አደባባይ እስከመውጣት ደርሷል። ስለአፈር ብዙ ቢነገርም አፈር እህል ለማብቀል የሚያስችል የተፈጥሮ ፀጋ ያለው ትልቅ ሀብትነቱ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል። በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ትምህርት ዘርፍ የአፈር ለምነት ተመራማሪው ፕሮፌሰር እንየው አድጎ ስለአፈር ምንነት ያስረዳሉ።

ምስል Shewangizaw Wogayehu/DW

 ሸዋዬ ለገሠ 

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW