1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና ቻይና፣

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2005

ጆሃንስበርግ ፣ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በተካሄደ የአፍሪቃውያንና የቻይና የመሪዎች ጉባዔ፣ የዝምባባዌ ምክትል ጠ/ሚንስትር፣ አርተር ሙታምባራ፣ አፍሪቃውያን ከቻይና ጋር በሚኖራቸው የኤኮኖሚ ግንኙነት የራሳቸውን ጥቅም ማስጠበቂያ መርኅ እንዲከተሉ

ምስል AP

አስገነዘቡ። ሚንስትሩ ፣ አብዛኞቹ የአፍሪቃ አገሮች ነጻነታቸውን ከተቀዳጁ ከ 50 ዓመታ ት በላይ ሆኖ ሳለ ፣ ለአሁኑ የኤኮኖሚ ድቀት፤ ቤይጂንግን ፤ አፓርታይድንም ሆነ ቅኝ አገዛዝን ሰበብ አድርጎ ማቅረብ ግብዝነት መሆኑን ሳያስጠነቅቁ አላለፉም። የዝምባባዌው ምክትል ጠ/ሚንስትር አፍሪቃውያን ለራሳቸው ጥቅም በሚበጅ መልኩ ከቻይና ጋር መደራደርም ሆነ መዋዋል እንዳለባቸው አሳስበዋልና ፤ ሚንስትሩ በግልጽ ቋንቋና በድፍረት ያቀረቡት ማስገንዘቢያ እንዴት እንደሚታይ ፣ በፀጥታ ጉዳዮች ተቋም የምሥራቅ አፍሪቃ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑትን ምስተር አንድርውስ አታ አሳሞዋን ጠይቄአቸው ነበር።«ምክትል ጠ/ሚንስትሩ ያሰሙት ከዚህ ቀደም ተደማጭነት ያላቸው ተዋንያን፣ ተንታኞችና አፍሪቃውያን የከፍተኛ ተቋማት ምሁራን ባለፉት ዓመታት ለአፍሪቃውያን መሪዎች ሲያገነዝቡ የነበረውን ጉዳይ ነው

ምስል AP

ቻይና ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለአፍሪቃ የልማት ግቦች ይበልጥ ጠቃሚ ተጓዳኝ እየሆነች መምጣቷን ከማሳሰብ አልቦዘኑም ነበር። ይሁን እንጂ ያየነው ምንድን ነው----አፍሪቃ ተባብሮ በአንድ ድምጽ ከመናገር ይልቅ ከቻይና ጋር በተናጠል መዋዋል ሆኗል የተመረጠው። ምክትል ጠ/ሚንስትሩ ለማድረግ የሞከሩት፣ የአፍሪቃ አገሮች ለክፍለ ዓለሙ ጥቅም አንድ ሆነው በመቅረብ ፣ ከቻይና ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት፤ በጋራ የትብብር ውል አርቅቀው በአንድ ድምፅ ለመናገር መቅረብ መቻልም እንደማያዳግት ለማመላከት ነው።ጥሪው የቀረበበት ጊዜ በጣም ተፈላጊና ጠቃሚም ነው። ምንም እንኳ ፍጹም አዲስ የሚባል ጥሪ ባይሆንም በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ካለ ከአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር በመቅረቡ በጣም ተፈላጊ ነው።»

የዝምባባዌው ም/ጠ/ሚ አርተር ሙታምባራለመላው የአፍሪቃ አህጉር ነው ማሳሰቢያ ያቀረቡት። መደራደሪያ ነጥቦች ሲሉ አፍሪቃውያን ምን ይሆን ይዘው እንዲቀርቡ የሚጠበቀው አንድርውስ አታ አሳሞዋ ምላሽ አላቸው።

ምስል REBECCA BLACKWELL/AP/dapd

«የድርድር ነጥቦችን ጉዳይ ካነሣን ፣ መደራደሪያ ነጥቦች በትክክል ፣ ከጉዳይ -ጉዳይ ሊለያዩ ይችላሉ። ይህም ማለት ከቻይና ጋር ለመዋዋል በተናጠል ሳይሆን በጅምላ በአንድ ድምፅ ፤በኅብረት መቅረብ ነው። ይህ ካልሆነ፣ ከ 53 በላይ ለሆኑት የአፍሪቃ አገሮች አስቸጋሪ ነው። በተናጠል መዋዋል ካለም ቻይና ትሆናለች ይበልጥ የምትጠቀመው። እንደሚመስለኝ የዚህ አመክንዮ ግልጽ ነውና አፍሪቃውያን አስበው ሊንቀሳቀሱበት የሚገባ ጉዳይ ነው። »

የዝምባብዌው ም/ጠ/ሚ አርተር ሙታምባራ አፍሪቃውያን ፣ እንዲሁ ቤይጂንግን፤ «አፓርታይድ»ንም ሆነ የቀድሞ ቅኝ አገዛዝን ፣ ለአሁኑ ብልሹ የኤኮኖሚ አያያዝ ሰበብ እያደረጉ ማንሳት የለባቸውም ሲሉም አስገንዝበዋል። የተጠቀሱት 3 ነጥቦች የቱን ያህል አላግባብ ማመካኛ እየሆኑ ቀርበዋል ይላሉ?

«ለማንኛውም የአፍሪቃ ሀገር በሚያጋጥሙት ችግሮች (ከልማት አንጻር ማለት ነው)ቀላሉ ሰበብ ያለፈ የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ይሆናል። ይህ ደግሞ የተለመደ አላግባብ ማምለጫ ምክንያት እየሆነ ሲቀርብ ነው የሚሰማው። ኋላ-ቀርነትንና ከፊት የተደቀኑ ተግዳሮቶችን በተመለከተ በቅኝ አገዛዝ የሚያላክኩ ፣

ብዙዎች አገሮች ናቸው። ሚንስትሩ፣ የአፍሪቃ መሪዎች ብዙዎቹን የክፍለ-ዓለሙን ችግሮች ለመፍታት ባለፉ የቅኝ አገዛዝ ታሪኮች ላይ ከማትኮር ይልቅ ለወደፊቱ የሚገባውን ማድረግ እንደሚገባቸው ነው

ያስገነዘቡትአፍሪቃ ፣ ዛሬ ለምትገኝበት ሁኔታ፤ ቅኝ አገዛዝ የራሱ አስተዋጽዖ ቢኖረውም እንደሚመስለኝ፤ የአፍሪቃ መሪዎች ያለፈውን ችላ በማለት ቀጣይነት ላለው ልማት እንዲታገሉ ነው ጥሪ የሚቀርብላቸው።»

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW