1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃዊቷ ሞሮኮ በአስደማሚ የኳስ ጥበብ ስፔንን አሸነፈች!

ማክሰኞ፣ ኅዳር 27 2015

ስፔን እና ሞሮኮ በቀጠር የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ዛሬ ባደረጉት የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ መደበኛው 90 ደቂቃም ሆነ ጭማሪው 30 ደቂቃ ያለምንም ግብ ተጠናቆ በፍጹም ቅጣት ምት ሞሮኮ አሸናፊ ሆኗል። የሞሮኮ ደጋፊዎች ድጋፍ እጅግ ደማቅ እና ብርቱ ነበር።

WM FIFA 2022 | Achtelfinale | Marokko vs Spanien
ምስል Javier Garcia/Shutterstock/IMAGO

ስፔን እና ሞሮኮ በቀጠር የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ዛሬ ባደረጉት የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ መደበኛው 90 ደቂቃም ሆነ ጭማሪው 30 ደቂቃ ያለምንም ግብ ተጠናቆ በፍጹም ቅጣት ምት ሞሮኮ በአውሮጳ ጠንካራውን የስፔን ቡድን 3 ለ0 ድል አድርጋለች። የሞሮኮ ደጋፊዎች ድጋፍ እጅግ ደማቅ እና ብርቱ ነበር።

በዚህ ውጤት መሠረትም ሞሮኮ ዘንድሮ አፍሪቃን ወክለው ለዓለም ዋንጫ ከቀረቡ አምስት ሃገራት መካከል ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፈች ብቸኛ ሀገር ሆናለች። ከጥቂት ሰአታት በኋላ ደግሞ ፖርቹጋል ከስዊትዘርላንድ ጋር ይጋጠማሉ። ከፖርቹጋል እና ስዊትዘርላንድ አሸናፊ ጋር በሩብ ፍጻሜው ሞሮኮ የፊታችን ቅዳሜ ትጋጠማለች። ያን ጨዋታም ካለፈች ወደ ግማሽ ፍጻሜው በመሻገር የመጀመሪያዋ አፍሪቃዊት ሀገር የመሆን ክብር ትቀዳጃለች ማለት ነው።

የስፔን አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በጨዋታው ወቅት የሞሮኮ ተጨዋቾች ሰአት እያባከኑ ነው በሚል ሰአታቸውን ዕያሳዩ ሲበሳጩ ነበር። የፍጹም ቅጣት ምት መለያው ነገር ቀድሞም የታያቸው ይመስላል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW