አፍሪቃውያን ስደተኞችና የእሥራኤል ውሳኔ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2004ማስታወቂያ
ከእሥራኤል ሕዝብ እና ካንዳንድ የገዢው ፓርቲ አባላት ብርቱ ተቃውሞ ከተነሳ በኋላ ነበር ግፊት የጠነከረበት ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሚመሩት መንግሥት ከትናንት ወዲያ ይህን ውሳኔ የወሰደው። የሀይፋው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ እንደገለጸልን፡ በውሳኔው መሠረት፡ የመመለሱ ሂደት በሁለት ዙሮች የሚከናውን ሲሆን፡ በመጀመሪያው ዙር ወደ ሀገራቸው የሚመለሱት ስደተኞች ቁጥር ሀያ አምስት ሺህ ነው።
ግርማው አሻግሬ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ