1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አፍሪቃ፤ ሽብርተኝነትን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት 

ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2011

አፍሪቃ ከሚያጋጥማት የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ፤ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እንዲሁም የእርስ በርስ ጦርነትና ማቆምያ የታጣለት የሕዝቦችዋ አስከፊ ስደት ወደፊት አላላዉስ ካላት የድህነት አረንቋ ላለመውጣቷ እንደምክንያት ይጠቀሳል።

Infografik Karte Verbreitung von Mobilfunkverträgen in Afrika mit Ländernamen DEU

የሽብርተኝነት መስፋፋት የአህጉሪቱ ሌላዉ ፈተና ሆንዋል

This browser does not support the audio element.

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሊቢያ በሳህል ቀጣና አገሮች እንዲሁም በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሃገራት የሚታየዉ የሽብርተኝነት መስፋፋት የአህጉሪቱ ሌላዉ ፈተና እንደሆነ ተመልክቶአል። ይህ በሽብርተኞች በሚፈፀም ድንገተኛ ጥቃት የበርካታ ንፁሐን ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ንብረት እያወደመም ነዉ። በሃገራት አካባቢያዊ የጥምር ጦርና በተወሰኑ ምዕራባዉያንና በመካከለኛዉ ምሥራቅ ሃገራት መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመቆጣጠር ቢሞከርም አንዴ ሞቅ አንዴ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ ዛሬም ድረስ ሽብርተኝነት የአህጉሪቱ የደሕንነት ሥጋት መሆኑን ቀጥሏል ተብሏል። የአፍሪቃን ፀጥታና አስተዳደር እንዲሁም በአህጉሪቱ የሚታየዉ የፅንፈኝነት እውነታና ሥረ መሠረትን የዳሰሰ ዓለም አቀፋዊ ጉባዔ ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ ተካሂዶ ነበር። በጉባዔዉ በርካታ የጥናት ፅሑፎች የቀረቡ ሲሆን ፤ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሁሉም ትብብር ተጠይዋል። 


ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW