አፍሪቃ ከፖሊዮ «ነፃ» ወጣች
ረቡዕ፣ ነሐሴ 20 2012
ማስታወቂያ
የልጅነት ልምሻ ወይም ፖሊዮ ከመላዉ አፍሪቃ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት አረጋገጠ።ድርጅቱ እንዳለዉ የልጅነት ልምሻ አፍሪቃ ዉስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የታየዉ የዛሬ አራት ዓመት ግድም ናጄሪያ ዉስጥ ነበር።ከዚያ በኋላ በተከታታይ በተሰጠዉ ክትባት በየዓመቱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ለአካለ ጎዶሎነት ከሚዳርገዉ በሽታ አፍሪቃ ነፃ መሆንዋ ተረጋግጧል።ይሁንና በሽታዉን የሚያመጣዉ ተሕዋሲ ዳግም ሊያንሰራራ ስለሚችል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ።የልጅነት ልምሻ አሁንም አፍቃኒስታንና ፓኪስታን ዉስጥ መኖሩን የዓለም ጤና ድርጅት አስታዉቋል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ