አፍጋኒስታን ውስጥ ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር ተሰልፎ የነበረ አፍጋናዊ ዋሽንግተን ውስጥ ወታደሮች
ሐሙስ፣ ኅዳር 18 2018
ዩናይትድስ ስቴትስ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ በነጩ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ አንድ አፍጋናዊ ሁለት የብሔራዊ ዘብ አባላት ላይ ትናንት ተኩስ ከፍቶ በጽኑእ ማቁሰሉ ተነግሯል ። ጥቃቱን አደረሰ የተባለው ራማኑላህ ላካናዋል በመባል የሚታወቅ የ29 ዓመት አፍጋናዊው መሆኑ ተገልጧል ። ተጠርጣሪው አፍጋኒስታን ውስጥ ካንዳሃር አቅራቢያ ሰፍረው ከነበሩ የዩናይትድ ስቴትስ የልዩ ኃይል ወታደሮች ጋር ተሰልፎ ለዐሥር ዓመታት ግድም ያገለገለ መሆኑም ተጠቅሷል ። ጥቃት ካደረሰ በኋላ ተተኩሶበት በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ለዩናይትድ ስቴትስ ተባባሪ ለነበሩ አፍጋናውያንን በተሰጠ እድል እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2021 ዩናይትድ ስቴትስ መግባቱም ተዘግቧል ። ስለዚህ የተኩስ ሩምታ በመክፈት ጥቃቱን ስላደረሰው ሰው ማንነት ሌላ ምን የሚታወቅነገር አለ? ስለዚህ የተኩስ ሩምታ በመክፈት ጥቃቱን ስላደረሰው ሰው ማንነት ሌላ ምን የሚታወቅነገር አለ?
ታሊባን በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እና ጥበቃ ሲደረግለት የነበረውን መንግሥት አስወግዶ አፍጋኒስታንን ሲቆጣጠር በርካታ የአሜሪካ ደጋፊዎች መገደላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ መሰደዳቸው ይታወቃል ። ጥቃቱን ያደረሰው አፍጋናዊ የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን በተተራመሰ መልኩ ከወጣ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ የገባ መሆኑ ተገልጧል ። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቃቱን «የሽብር ጥቃት» ብለውታል ። ስለ ጥቃቱ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር አለ?
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከእርሳቸው በፊት በቀድሞው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዘመን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የገቡ አፍጋናውያን በአጠቃላይ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ አዝዘዋል ። ፓኪስታን ውስጥ የሚገኙ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ አፍጋናውያን እጣ ፈንታም እጅግ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ። በአጠቃላይ በተለይ የአፍጋናውያን ብሎም የሌሎች አገራት የጥገኝነት ጥያቄ ላይ ይህ የትናንቱ ጥቃት ምን ተጽእኖ ይፈጥራል ተባለ?
ማንተጋፍቶት ስለሺ/ ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ