1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራናዉያን፤ እገዳዉን ጥሰዉ ሰልፍ ወጡ

ረቡዕ፣ የካቲት 9 2003

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወኑ የዲሞክራሲ ንቅናቄዎችን በመደገፍ ትናት ሰኞ ሰልፍ መውጣታቸው ተዘገበ።

ምስል AP

ከሰልፈኞቹ መካከል የሞተ ሰው እንዳለ በርካቶቹም ጭንቅላታቸውን ንዝረት በሚፈጥር ዱላ እንደተደበደቡ ተጠቅሷል።

የአይን ምስክሮች እንደገለፁት ከሆነ ትናንት በኢራን በተከናወነው ሰልፍ ሶስት ስልፈኞች በጥይት ተመትተው ሆስፒታል ገብተዋል። አንድ ሰው መሞቱም ታውቋል። ለመንግስት ቅርበት እንዳለው የሚነገርለት fars.com የተሰኘው ድረ-ገፅ ለንባብ እንዳበቃው ከሆነ ደግሞ፤ በርካታ አላፊ አግዳሚዎች ጭንቅላታቸው ላይ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል። እንደ አይን ምስክሮች ከሆነ ትናንት የቴህራን ጎዳናዎች ለቁጥር በሚያታክቱ የፀጥታ ሀይላት ተጥለቅልቀው ነበር። አንድ ኢራናዊ ወጣት የሚከተለውን ለዶቼ ቬሌ ገልጿል።

የሚሊሺያዎቹ ብዛት እጅግ በጣም ያስደነግጣል። በእርግጥ ህፃናትንም መመልመላቸው ግልፅ ነው። ዱላ የያዙ አለያም ሞተር ቢስክሌቶች ላይ የተቀመጡ የአስር እና የአስራ አንድ ዓመት ታዳጊዎችን ማየት ይቻላል። አላፊ አግዳሚውን እያስቆሙ ወዴት እንደሚሄድ ይጠይቁ ነበር።

ትናንት በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን የተከናወነው ሰልፍ ዋነኛ ዓላማ በግብፅና ቱኒዚያ ለተከናወኑ ሰልፎች ድጋፍ ለመስጠት እንደነበረ ታውቋል። ሆኖም ሰልፈኞቹ ሞት ለአምባገነኖች እያሉ ይፈክሩ እንደነበረም ተጠቅሷል።

ሰልፈኞቹ ጥቂት በጥቂት በመሆን በአብዛኛው በፀጥታ ተውጠው መሰባሰብ ያዙ። ፖሊሶች ሰልፈኛውን በአይነ ቁራኛ እየጠበቁ ነው። በኢራን እጅግ እንደሚፈራ የሚነገርለት የባሲጅ ሚሊሺያ ግን ወደ ሰልፈኛው መሀል በመዝለቅ ህፃን ሽማግሌ ሳይል ንዝረት በሚፈጥር የኤሌክትሪክ ዱላ መቀጥቀጡን ተያያዘው። ግርግሩን አምልጠው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቤት የተጠለሉ አንድ የሰባ ዓመት አዛውንት ሁኔታውን ማብራራታቸውን ይቀጥላሉ።

ምስል Kosoof

ትንፋሽ ነበር ያጠረኝ። በእርግጥ «ሞት ለአምባገነኖች» እያሉ የሚጮሁ በርካታ ሰዎች በየጎዳናው አሁንም አሉ። በዚያው መጠን ደግሞ ሚሊሺያዎቹ ምህረት አልባ በሆነ መልኩ ሰዉን ንዝረት በሚፈጥር የኤሌክትሪክ ዱላ እየቀጠቀጡት ነው። በሰልፈኞቹ በኩል ጥግ ጥጉን ይዘው ያልፉ የነበሩ አንዲት ባልቴትንም እንዲሁ ደብድበዋቸዋል።

የትናቱን ሰልፍ ተከትሎ የኢራን መንግስት ድርጊት በብዙዎች ዘንድ አስተዛዛቢ ሆኗል። የኢራን መንግስት በግብፅና በቱኒዚያ የተከናወኑ ህዝባዊ አመፆችን እንደሚደግፍ በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወቃል። በሀገሩ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በተመሳሳይ መልኩ ለግብፅና ቱኒዚያ ድጋፋቸውን ለማሳየት የጠሩትን ሰልፍ ግን አግዷል። ከዚያም አልፎ በተቃዋሚዎች የታቀደው ሰልፍ ይዘት በቀደደው ቦይ እንዲፈስለት መፈለጉም አልቀረም። የግብፅን የዲሞክራሲ ንቅናቄ «እስላማዊ አብዮት» በማለት ከጥቂት ቀናት በፊት መንግስት ሰልፍ ጠርቶ ነበር። ታዲያ በሰልፉ ላይ ተቃዋሚዎችም እንዲገኙ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ እንደነበረም ተጠቅሷል። ከዚያ ውጪ ግን የትናንቱ ሰልፍ እንዲካሄድ የኢራን መንግስት ፈፅሞ አልፈቀደም።

እገዳውን ጥሰው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች አደባባይ ሲወጡ፤ መንግስት ወዲያውኑ የተንቀሳቃሽ ስልኮችን፣ ኢንተርኔትንና የተቃዋሚ ድረ-ገፆችን ከአገልግሎት ውጪ አድርጓቸዋል። ተንቀሳቃሽ ስልኮችና ኢንተርኔት የፕሬስ ነፃነት በሌለባት ኢራን ተቃውሞን ለመግለፅ በዋነኛ ልሳንነት ማገልገላቸው ይታወቃል። የኢራን ወታቶች በአንፃሩ መንግስት በብቸኛነት ፕሮፓጋንዳ የሚነዛባቸውን ድረ-ገፆች ማሰናከላቸውም ተዘግቧል። ይህንኑ አስመልክቶ አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የኮምፒውተር ጠበብት እንደገለፀው።

የኢራን የዜና ወኪል፤ IRIB.ir የተሰኘው ማለት ነው፤ ከእይታ ውጪ ነው። ያ ለኛ በዚህ ምሽት ትልቁ ስኬታችን ነበር። ለመንግስት ቅርበት ያላቸው አንዳንድ ድረ-ገፆችም እንዲሁ እንዳይታዩ አድርገናቸዋል። እንደ Rajanews.com እና Farsnews.com ያሉ ድረ-ገፆችን ከእይታ ውጪ ነው ያደረግናቸው። ምንም እንኳን በኢራን መንግስት አንፃር እቀባ ቢጣልም እንደነዚህ አይነቶቹ ድረ-ገፆች ግን ካናዳ አለያም ኦስትሪያ ውስጥ ሆነው ጠንካራ ድጋፍ የሚደረግላቸው ነበሩ።

የትናንቱን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የኢራ

ምስል AP

ን መንግስት በተቃዋሚ መሪዎች ላይ የሞት ቅጣት ለማስጠየቅ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ ታውቋል። በተያያዘ ዜና ትናንት በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አንድ የስፔን ዲፕሎማት በኢራን የፀጥታ ሀይላት ከመንገድ ተይዞ ለሰዓታት መታሰሩም ተዘገቧል። ሁኔታውን ስፔን በቸልታ እንደማታየውም ጠቅሳለች። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሀላፊ ካተሪን አሽቶን በበኩላቸው ሰልፈኞቹን በተመለከተ የኢራን መንግስት ሀይል ከታከለበት ርምጃ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ትናንት በኢራን የጀመረው ሰልፍ ወደፊት በሌሎች ቀናት ይቀጥል አይቀጥል የሚታወቅ ነገር የለውም።

ሻብናም ኑሪያን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW