1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሬቻ በፍራንክፈርት

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 2 2017

የኢሬቻ በዓል በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እና ጀርመናውያን ታዳሚዎች በተገኙበት ተከብሯል።

Deutschland I Frankfurt - Die Oromo-Gemeinschaft feierte das kulturelle Erntedankfest
ምስል privat

ኢሬቻ በፍራንክፈርት

This browser does not support the audio element.

ኢሬቻ ቢሾፍቱ ውስጥ በሚገኘው የሆራ ሀርሰዲ ሀይቅ  የኦሮሞ አባገዳዎች እና በሚልዮን የሚቆጠሩ ታዳምያን በተገኙበት ተከብሯል። ቀደም ሲልምኢሬቻ ሁራ ፊንፊኔ በአዲስ አበባ መከበሩ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እና ጀርመናውያን ታዳሚዎች በተገኙበት ተከብሯል። ከበአሉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ኤልያስ ኦፍጋቴሶ ለDW በሰጡት አስተያየት በዓለ በተለያዩ የአውሮጳ ከተሞች በዙር አንደሚከበር ገልጸው የዘንድሮ ተረኛ አስተናጋጅ የፍራንክፈርት ከተማ እንደሆነች ገልጸውልናል።

በጀርመን የቬስት ቫሊያ ራየን ላንድ የሚገኙ የኦሮሞ ማህበረሰብ እና ሌሎች በተገኙበት የኤሬቻ በዓልን ባለፈው ሳምንት በዱስልዶርፍ ከተማ ተከብሯል። በዓሉ በየዓመቱ በተመሳሳይ መልኩ እንደሚከበር ታዳሚያን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።  

ኢሬቻ በፍራንክፈርት ጀርመንምስል privat

በዓሉ ምስጋና ለፈጣሪ የሚቀርብበት ነው ያሉት አቶ ኤልያስ ከተለያዩ የጀርመን ግዛቶች የመጡ የኦሮሞ ብሔር አባላት ተገኝተው ሥነስርአቱን አድምቀውታል ነው ያሉት። የጀርመን የኦሮሞ ማሕበረሰብ አባላት ባሕላቸውን ለማቀብና ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነና በተለይ በጀርመን ተወልደው የሚያድጉ ሕጻናት ባሕላቸውንና ቋንቋቸውን እንዲያውቁና እንዲለምዱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አቶ ኤልያስ አክለዋል።

በዘንድሮውን የፍራንክፈርት የኢሬቻ በዓል ላይ ታዳሚዎች “ሆ..ያ..ማሬዎ…” እያሉ የምስጋና ቃል እያዜሙ በዓሉን እንዳከበሩትም ነግረውናል። አቶ ኤልያስን አነጋግረናቸዋል የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW