ኢሬቻ እና አዲሱ ትውልድ
ዓርብ፣ መስከረም 20 2009ማስታወቂያ
በመጪው እሁድ ከቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሆራ አርሰዲ ሐይቅ አጠገብ ኢሬቻ ይከበራል። ከአዲስ አበባ ደቡብ ምሥራቅ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ የሚከበረው በዓል ኢሬቻ መልካ ይሰኛል። በዕለተ እሁድ ኦ …. ያ…ማሬዎ….. ማሬዎ እያሉ ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን ከሚያከብሩት መካከል የ25ቷ ኩኑ አለማየሁ ትገኝበታለች።
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ሰኚ በላቸው ይህን በዓል ሲያከብር የዘንድሮው አራተኛው መሆኑ ነው። ለሰኚ ኢሬቻ ከምዕራባውያኑ የምሥጋና በዓል ጋር ተመሳሳይ ነው። በሰኚ አባባል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ኢሬቻን ለማክበር ሲሰበሰቡ ስላለፈው ይወያያሉ። ስለ ነገውም ይመክራሉ።
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሰ