1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመጉ ሽልማቱን በመጪው ግንቦት ይረከባል

ረቡዕ፣ መጋቢት 14 2014

ጀርመን በሚገኘው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚሰጠውን የ2022 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ሽልማት ያሸነፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሽልማቱን ግንቦት ወር በርሊን ላይ እንደሚቀበል ተገለጠ።

Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

ለ30 ዓመታት አስተዋጽኦ ዓለም አቀፍ እውቅና

This browser does not support the audio element.

ጀርመን በሚገኘው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚሰጠውን የ2022 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ሽልማት ያሸነፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሽልማቱን ግንቦት ወር በርሊን ላይ እንደሚቀበል ተገለጠ። ኢሰመጉ በየሁለት ዓመቱ የሚሰጠውን ሽልማት ያሸነፈው በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 30 ዓመታት ለድምፅ አልባዎች ድምፅ በመሆን፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለደረሰባቸው በመታገል ላበረከተው አስተዋጽዖ በሚል ነው። የኢሰመጉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳን ይርጋ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ሽልማቱ ተቋሙን ለበለጠ ሥራ የሚያበረታታ እና ሥራችን በሌሎች ዕንደሚታይ የሚያመላክት ዕውቅና ነው ብለዋል። ኢሰመጉ 10 ሺህ ዩሮ የሚጨምረውን ይህንን ሽልማቱን በቀጣይ ግንቦት ጀርመን ቤርሊን ከተማ ውስጥ ይረከባል።

ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW