1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመጉ በኢትዮጵያ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚፈጸም እስር አሳስቦኛል አለ

ሰኞ፣ ግንቦት 15 2014

ከቅርብ ግዚያት ወዲህ እየተበራከተ የመጣው የግለሰቦች የሰባዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰበው ኢሰመጉ አታወቀ። ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ግለሰቦች ከየቦታው ተጠልፈዉ ለተውሰኑ ቀናት የት እንደደረሱ አለመታወቁ እና ኃለፊነቱን የሚወስድ አካል አለመኖሩ ከፍተኛ የሰባዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የግለሰቦችን ህገ-መንግስታዊ መብትን መቃወም ነው ብልዋል።

Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

 

ከቅርብ ግዚያት ወዲህ እየተበራከተ የመጣው የግለሰቦች የሰባዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰበው የኢትዪጵያ ሰባዊመብት ጉባኤ (ኢሰመጉ ) አታወቀ። ኢሰመጉ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 15 ባወጣው መግለጫ ግለሰቦች ከየቦታው ተጠልፈው ለተውሰኑ ቀናት የት እንደደረሱ አለመታወቁ እና ኃለፊነቱን የሚወስድ አካል አለመኖሩ ከፍተኛ የሰባዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የግለሰቦችን ህገ-መንግስታዊ መብትን  መቃወም ነው ብልዋል። መግላጫው ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከቤታቸው  በወጡበት መታፈናቸውን፤ አቶ ናፖሊዮን ገ/እየሱስ ገብሩ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ  በታጠቁ ሁለት ሲቪሎች እና አራት ፖሊሶች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ  ታስሮ እንደነበር፣ጠቅሶአል። መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ፤ ጋዜጠኛ ታድዮስ ታንቱ ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ባለፈዉ ሳምንት በመንግሥት አካላት ከታሰሩ የማኅበረሰብ አንቂዎች እና የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ዜጎች መካከል ናቸዉ ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተደጋጋሚ ጊዜ በሸኔ ታጣቂዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በሚወሰዱ እርምጃዎች በበርካታ ንጹሀን ዜጎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት፣ ዝርፊያ እና መፈናቀል ሲደርስ መቆየቱንም ኢሰመጉ በመግለጫዉ አስታዉሶአል። ፡ ኢሰመጉ ባሰባሰባቸው መረጃዎች መሰረት እነዚህ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሁለቱም አካላት የተፈጸሙ መሆናቸውን ኢሰመጉ ለመረዳት ችሏል ብልዋል።

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW