ኢቦላ፣ የኅመሙ ምልክቶች
ዓርብ፣ የካቲት 13 2007ማስታወቂያ
ከወባ እና ከኢንፍሉዌንዛ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በዚህ ወቅት የሚታዩት የበሽታው ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ያልተለመደ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት
- ማቅለሽለሽ እና ትውከት
- ተቅማጥ
- የጉሮሮ ቁስለት
- ራስ ምታት
- የጡንቻ ኅመም
- የጨጓራ ኅመም
- ዝለት
- የምግብ ፍላጎት እጦት
እነዚህ ሁሉ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፤ ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ምልክቶች አንዱ አለያም ኹለቱ ብቻም ሊታይባቸው ይችላል። የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች ከታዩ ከአምስት ቀናት በኋላ በሰውነት የመተንፈሻ አካላት ቀዳዳዎች በኩል መድማት ሊከሰት ይችላል። ይኽ መድማት እንደ አፍ፣ አፍንጫ እና የመራቢያ አካላት ባሉ የሰውነት ቀዳዳዎችም ሊከሰት ይችላል።