1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያን ጨምሮ 26 ሃገራት የከፋ የብድር አዘቅት ውስጥ ይገኛሉ ተባለ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 7 2017

የዓለም ባንክ ከሰሞኑ ባወጣው አዲስ ዘገባ ኢትዮጵያን ጨምሮ 26 ሃገራት ባለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት ውስጥ የከፋ የብድር አዘቅት ውስጥ እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል ። የተጠቀሱት ሃገራት እጅግ ደካማ ኤኮኖሚ እንዳላቸው ተገልጧል ።

USA, Washington | Hauptsitz der World Bank Group
ምስል Daniel Slim/AFP/Getty Images

በጣም ደሐ የተባሉት 26ቱ ሃገራት

This browser does not support the audio element.

የዓለም ባንክ ከሰሞኑ ባወጣው አዲስ ዘገባ ኢትዮጵያን ጨምሮ 26 ሃገራት ባለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት ውስጥ የከፋ የብድር አዘቅት ውስጥ እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል ። የተጠቀሱት ሃገራት እጅግ ደካማ ኤኮኖሚ እንዳላቸው ተገልጧል ። በዋናነት የኮቪድ 20 ወረርሽኝ መቀስቀስ እና ግጭቶች የሃገራቱን ኤኮኖሚ ይበልጥ ማድቀቃቸውም ተጠቁሟል ።

የዓለም ባንክ ከሳምንት በፊት ባወጣው ዘገባ በጣም ደሀ ሲል በዘረዘራቸው 26 ሃገራት ውስጥ 40 ከመቶ ነዋሪዎች የቀን ገቢያቸው ከ2,15 ዶላር በታች ነው ብሏል ።  ይህ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? የኢኮኖሚ ምሑሩ ኢሜረተስ ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ፦የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2023 የተስማሙበትን የኢትዮጵያ እና የኬንያን የኑሮ ሁኔታ መረጃ አነጻጽረዋል ።  የዓመታዊ የኤኮኖሚ እድገቱን በማስቀደም ይጀምራሉ ።

«የኢትዮጵያ $890 ዶላር ነው፥ የኬንያ $1,800 ዶላር ነው ኢትዮጵያ ዓመታዊ የኤኮኖሚ እድገቷ 7.9% ኬንያ 5.2% አደገች ይላል የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ 30% በኬንያ 7.7% ገደማ ይላል የኢትዮጵያን የኤኮኖሚ እድገት እና የገባያ ግሽበት ስታወዳድር የኢትዮጵያ የኑሮ ደረጃ 26% የኬንያ 3%  ወደታች አሽቆልቁሏል ስለዚህ የኢትዮጵያን ሕዝብ የኑሮ ጭንቀት፤ ችግር በዚህ ታያለህ ማለት ነው »

አንዳንድ ተንታኞች፦ የዓለም ባንክም ሆነ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ያስቀመጡት የኤኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ ለችግሩ ሰበብ ነው፤ ይህን ግን ዓለም ዓቀፍ ተቋማቱ አይገልጡም ሲሉ ይደመጣል ። ፕሮፌሰር ዳንኤል፦ ብዙዎች በኢትዮጵያ የገንዘብ ምንዛሬ ለውጥ መደረጉን ከኤኮኖሚ ለውጥ ጋር ያምታታሉ ሲሉ መታረም እንዳለበት ጠቁመዋል።  

«ከዓለም ባንክ ጋር ያደረጉት ውል የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ነው እንጂ የኤኮኖሚ ፖሊሲ አይደለም ከተለያዩ ዜና ማሰራጫዎች ላይ ስመለከት የተሳሳተ አነጋገር አለ ኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ፖሊሲዋን አልቀየረችም፥ ምንዛሬ ፖሊሲ ነው የተቀየረው »

የዓለም ባንክ የኤኮኖሚ ምክትል ኃላፊ አያህን ኮሴ፦ «ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት ለራሳቸው ሊያደርጓቸው የሚገቡ እና ማድረግም የሚችሏቸው ጉዳዮች አሉ » ብለዋል።  የታክስ/ግብር አሰባሰብ ስልታቸውን ማስተካከል እና ማስፋት፤ የመንግሥት ወጪዎችን መቀነስ የመሳሰሉት ተግባራትንም እንደመፍትኄ ጠቁመዋል ። ፕሮፌሰር ዳንኤል፦ ኢትዮጵያ የምንዛሬ ለውጥ ብታደርግም ተጠቃሚ አትሆንም ብለዋል ።  ምክንያታቸውን ሲያብራሩም ።

የዓለም ባንክ፤ ዋሽንግተን ዲሲምስል Andrew Harnik/AP/picture alliance

«የኢትዮጵያ የቡና፤ የቆዳ፤ የአበባ ፍላጎት በዓለም ገበያ የተወሰነ ነው በዓለም ገበያ መኪና አይደለም፤ ልብስ አይደለም፤ የቴክኖሎጂ እቃዎች አይደለም ኢትዮጵያ የምትልከው ኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ፖሊሲዋን መቀየር አለባት ነው፥ የምንዛሬ ፖሊሲ አይደለም ችግሩ »

የዓለም ባንክ ከዘረዘራቸው 26ቱ ሃገራት መካከል  ከአራቱ በስተቀር ሌሎቹ አፍሪቃ ውስጥ የሚገኙ ሃገራት መሆናቸውም ታውቋል ። አራቱ ከአፍሪቃ ውጪ ያሉ ሃገራት፦ አፍጋኒስታን፤ የመን፤ ሶሪያ እና ሰሜን ኮሪያ ናቸው ብሏል ። ከኢትዮጵያ ተጎራባች ከሆኑ ሃገራት መካከል ደግሞ ከንዑሷ ጅቡቲ እና ኬንያ በስተቀር ሌሎቹ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ26ቱ ሃገራት ውስጥ እንደሚመደቡ ተገልጧል ። ኢትዮጵያ፤ ኤርትራ፤ ሶማሊያ፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ሻገር ሲልም ርዋንዳ እና ብሩንዲ በምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ በዓለም ባንክ የደኸየ ኤኮኖሚ ያላቸው ተብለው የተፈረጁ ሃገራት ናቸው ።

ከኢኮኖሚ ምሑሩ ኢሜረተስ ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW