ኢትዮጵያዉን ከሱዳን ተባረሩ
ዓርብ፣ መጋቢት 3 2013
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ዳፋዉ ሱዳን ለሚኖሩ ኢትዮጵያንም እየተረፈ ነዉ።የሱዳን በተለይም ገዳሪፍ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት ዉዝግቡ ከተካረረ ወዲሕ የሱዳን ታጣቂዎች ኢትዮጵያዉያንን እየደበደቡና እየዘረፉ ከየሚኖሩበት አካባቢ እያበረሯቸዉ ነዉ።የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እንዳስታወቀዉ ባለፉት ወራት በሱዳን ታጣቂዎች የተባረሩ 230 ኢትዮጵያዉያን ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ተገድደዋል።ከተባረሩት ኢትዮጵያዉያን አንዳዶቹ እስከ 30 ዓመት ድረስ ሱዳን ዉስጥ የኖሩ ናቸዉ።መተማ-ዮሐንስ በተባለዉ አካባቢ የሠፈሩት ተባራሪዎች የመጠለያና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ችግር እንዳለባቸዉ አስታዉቀዋልም።የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን እንደዘገበዉ ከሱዳን የተባረሩት አብዛኞቹ የአማራ ተወላጆች ናቸዉ።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ