ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችና የመንግሥት ዕቅድ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2007ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ወደ ሐገራቸዉ ቢመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት የተለያዩ እግዛዎችን እንደሚያደርግ የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ እንዳስታወቁት ደቡብ አፍሪቃ ና ሊቢያ በሚኑሩ ኢትዮጵያዉን ላይ አሰቃቂ ግድያ ከተፈፀመ ወዲሕ ስደተኞቹን ለመቀበል እየተዘጋጀ ነዉ። አደገኛ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን በፈቃዳቸዉ ወደ ሐገራቸዉ ለመመለሰም ዝግጅት ላይ ነዉ።ቃል አቀባዩ የዝግጅቱን አይነትና የደረሰበትን ደረጃ ግን አልገለፁም። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ