1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ባህልሰሜን አሜሪካ

ኢትዮጵያዉያን እና የምስጋና ቀን አከባበር

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2016

«ኢሬቻ፤ ግንቦት ልደታ «ታንክስ ጊቪንግ» ነዉ በኢትዮጵያ። በየሳምንቱ ማህበር፤ ሰንበቴ እያልን የምንሰባሰብበት የምስጋና መድረካችን እኮ ነዉ። እነዚህ ባህሎቻችን በሙሉ፤ ከአሜሪካዉ «ታንክስ ጊቪንግ» በፊት የነበሩ ናቸዉ። አገራችን ኢትዮጵያ፤ እጆችዋን ወደ አምላክዋ ትዘረጋለች የሚል ታሪክ ነዉ ያላት።»

ዘጠኝ የኢትዮጵያ የግብረ- ሰናይ ተቋማት የጥምረት እርዳታ በምስጋና በዓል-አትላንታ 
ዘጠኝ የኢትዮጵያ የግብረ- ሰናይ ተቋማት የጥምረት እርዳታ በምስጋና በዓል-አትላንታ ምስል Thewodros Tadesse/DW

«ኢሬቻ እኮ «ታንክስ ጊቪንግ» ነዉ በኢትዮጵያ። ግንቦት ልደታ እኮ የምስጋና ቀን ነዉ በኢትዮጵያ። በየሳምንቱ በማህበር፤ የምንሰባሰብበት «ታንክስ ጊቪንግ» መድረካችን እኮ ነዉ።»

This browser does not support the audio element.

በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘዉ በሲምሶንያን ኢንስቲትውት በተፈጥሮ ሳይንስ ሙዝየም ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዮሃንስ ዘለቀ «ኢሬቻ እኮ «ታንክስ ጊቪንግ» ሲሉ ይናገራሉ። ዶክተር ዮሃንስ በኢትዮጵያ በብሔራዊ ደረጃ በተቋቋመዉ ዓለም አቀፍ የቅርስ አስመላሽ ኮሜቴ አባል ጭምር ናቸው። 

ዶክተር ዮሃንስ «ግንቦት ልደታ እኮ የምስጋና ቀን ነዉ በኢትዮጵያ። «ታንክስ ጊቪንግ» እኮ በየሳምንቱ ማህበር፤ ሰንበቴ እያልን የምንሰባሰብበት የምንጠጣበት የምንበላበት የምንፀልበት ምስጋና የምናቀርብበት እኮ መድረካችን ነዉ። እነዚህ ባህሎቻችን እኮ በሙሉ፤ ከአሜሪካዉ «ታንክስ ጊቪንግ»  በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩ ናቸዉ። የማንለዉጣቸዉ ባህሎቻችን ናቸዉ» ሲሉ ተናግረዋል። 

«ይህ ከ 30 እና 40 ዓመት ወዲህ የመጣዉ ፖለቲከኛ ግን፤ ይህ የክርስትያን ነዉ፤ ይህ የኢስላም ነዉ፤ ይህ የኦሮሞ ነዉ፤ ይህ የአማራ ነዉ ፤ ይህ የከንባታ ነዉ እያለ፤ የነበረንን ባህል እና የምስጋና ቀናት ሁሉ አጠፋብን።  አገራችን ኢትዮጵያ፤ እጆችዋን  ወደ አምላክዋ ትዘረጋለች የሚል ታሪክ ነዉ ያላት። ከማንኛዉም የዓለም ሃገራት የምስጋና ቀን ያለት የመጀመርያዋ ሃገር ኢትዮጵያ ናት» በማለት ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። 

በጎርጎረሳዉያኑ ቀን ቀመር ህዳር ወር አራተኛ ሳምንት ሃሙስ እለት በሰሜን አሜሪካ የሚከበረዉ «ታንክስ ጊቪንግ» ማለት የምስጋና ቀን ብሔራዊ በዓል ነዉ። ዘንድሮም በድምቀት ነዉ የተከበረዉ። ይህ ዕለት በዩናይትድ ስቴትስ ፤ቤተሰብ ጓደኛ የሚገናኝበት፤ በአቃፊ በአልነቱም ይታወቃል። በዓመት ዉስጥ ተራርቆ የነበረ ቤተሰብ ጓደኛ ከአለበት የሚሰባሰብበት ፤ በጋራ እራት የሚቋደስበት፤ ፈጣሪን በጋራ የሚመሰገንበት በዓል ነዉ። በዩናይትድ ስቴትስ በብሔራዊ ደረጃ የሚከበረዉ የምስጋና ክብረ በዓል፤ ሲዳረስ በሃገሪቱ ዙርያ በሚገኙ አዉራጎዳናዎች እና  የአየር ማረፍያዎች በተጓዦች ይጨናነቃሉ።

ታንክስጊቪንግ - የምስጋና በዓል አከባበርምስል Andrew Harnik/AP Photo/picture alliance

በክብረ በዓሉ እለት፤ የዳክዬ ጥብስ የድንች ስኳር እና የድፍን ባቄላ አደንጓሪ ወጥ በአሜሪካዉያኑ የምግብ ጠረቤዛ ላይ ይቀርባል። ይህ ባህል የመጣዉ በጥንት ግዜ አዉሮጳዉያን ወደ አሜሪካ ፈልሰዉ ሲገቡ ሬድ ኢንድያንስ የሚባሉት ነባር አሜሪካዉያን፤ መራባቸዉን አይተዉ ይህንን አይነት ምግብ ስላቀረቡላቸዉ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ።

የታሪክ አዋቂዉ እና በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘዉ የሲምሶንያን ኢንስቲትውት የተፈጥሮ ሳይንስ ሙዝየም ተመራማሪዉ ዶክተር ዮሃንስ ዘለቀ በዩናይትድ ስቴትስ ስለሚከበረዉ የምስጋና በዓል ጥንታዊነት ተናግረዋል። 

በ1620 ከአዉሮጳ የተጓዙ ሰዎች ወደ ዛሬዋ ዩናይትድ ስቴትስ ሲገቡ፤ በሕይወት የመኖራቸዉ ምክንያት በቫምፓኖግ ተወላጆች ወይም ሬድ ኢንዲያንስ በሚባሉት ነዋሪዎች ርዳታ በመሆኑ እንደሆን ይነገራል። ይህም የምስጋና ቀን ወይም «ታንክስጊቪንግ ቀን» ለመሰየሙ ምክንያት ሆንዋል ይባላል። አከባበሩ የጀመረዉ ግን ከዝያን ወቅት ከ200 ዓመታት በኋላ እንደነበር የታሪክ መዝገባት ያሳያሉ። ዶክተር ዮሃንስ ዘለቀ እንደሚሉት ይህን በዓል በመጀመርያ ተቀባይነት ያገኘዉ በክርስትና ሃይማኖት ተከታዩ ዘንድ ነዉ።

ግን እንደዉ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የኢትዮጵያዊ እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊን ቁጥር እጅግ ብዙ መሆኑ ይታወቃል። ታድያ ይህን ቀን እንዴት ነዉ የሚያከብሩት?

ዶክተር ዮሃንስ ዘለቀ ምስል Yohannes Zeleke

«ከ 40 ዓመታት ወዲህ እለቱን ኢትዮጵያዉያን በድምቀት ነዉ የሚያከብሩት። ቀደም ሲል የአሞራ በአል ይሉት ነበር። አሁን ግን በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊዉ ቁጥሩ ጨምሯል።  ተጋብቷል፤ ሃገሪቱን ህግ  ተቀብሎ ራሱን አዋህዶ በመኖሩ አሁን አሁን በኢትዮጵያዉያን ዘንድም በጉጊት የሚከበር በዓል ሆኗል።

 

ይህ የምስጋና በዓል በአትላንታ በሚገኙ ዘጠኝ የኢትዮጵያ የግብረ- ሰናይ ተቋማት ለመጀመርያ ጊዜ በአንድ ላይ በመቀናጀት "ካስማ" የተሰኘ ህብረት ፈጥረው በአትላንታ ከተማ ዉስጥ ለሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች እና ችግረኞች ምሳ አብልተዋል፤ የአልባሳት ርዳታም አድርገዋል።

እርዳታዉን ካሰባሰቡት ድርጅቶች መካከል « ተስፋ ለኢትዮጵያ» የተባለዉ አትላንታ በቀል ድርጅት ይገኝበታል ። ተስፋ ለኢትዮጵያ ከተቋቋመ 15 ዓመታትን አስቆጥሯል። ዘንድሮ የምስጋናን ቀንን ማለት ታንክስ ኪቪንግ ዴይን ለማክበር ሲዘጋጅ ድርጅቱ በኢትዮጵያ እየሰራቸዉ ያሉትን ስራዎች በመቃኘት ነዉ።

«ድርጅቱ ሲፀነስ በኢትዮጵያ በዳዉሮ አካባቢ 49 ሺህ ዶላር ወጭ አዉጥቶ ሰባት የዉሃ ጉድጓዶችን አስቆፍሮ አካባቢዉ ላይ ለሚኖሩ 2000ሺህ አባወራዎች ለመጀመርያ ጊዜ ንጹህ የመጠጥ ዉኃ አገልግሎትን አቅርቧል። ከዚህ በተጨማሪ « ተስፋ ለኢትዮጵያ» የተባለዉ አትላንታ በቀል ድርጅት  በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተዉ ረሃብ ርዳታን ሰጥቷል።

በዓመቱ ገንዘብ በማሰባሰብ እስካሁን ለ 13 ሺህ ህጻናት የትምህርት መገልገያ መሳርያን አቅርቧል። በአሁኑ ሰአት ለ 50 ኢትዮጵያዉያን ህጻናት የምግብ የልብስ እና የትምህርት ወጫቸዉን በቋሚነት በመቻል፤ በማሳደግ ላይ ይገኛል።  ከዚህ ሌላ  በዝያዉ በአትላንታ ዉስጥ የሚገኙ ችግረኛ ኢትዮጵያዉያን የሞያ ድጋፍ እንዲያገኙ፤ ብሎም  በህመም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እገዛ እንዲያገኙ አስችሏል።

ተስፋ ለኢትዮጵያ / የቦርድ አባላትምስል Thewodros Tadesse/DW

በአትላንታ የሚገኘዉ « ተስፋ ለኢትዮጵያ»  በተጓዘባቸዉ አስራ አምስት ዓመታት ብዙ ዉጣ ዉረዶችን በማሳለፉ፤ ከቅርብ ሳምንታት በፊት «የጽድቅ እና የጽናት ዓመታት» በሚል መሪቃል የመሰባሰብያ እና የምስጋና ምሽን ምሽት አካሂዶ ነበር።»

 

በዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች በጋራ የሚከበረዉ የምስጋና በዓል ባህልን ወደ ኢትዮጵያ ብንወስደዉ ምን ይለናል? ወይስ እኛ ኢትዮጵያዉያን የራሳችን የምስጋና ቀናት አሉን? ስንል ለዶ/ር ዮሃንስ ዘለቀን ጠይቀናቸዉ ነበር። 

ዘጠኝ የኢትዮጵያ የግብረ- ሰናይ ተቋማት የጥምረት እርዳታ በምስጋና በዓል-አትላንታ ምስል Thewodros Tadesse/DW

በአትላንታ የሚገኘዉ « ተስፋ ለኢትዮጵያ» ድርጅት የዘንድሮ የምስጋና በዓልን የጽድቅ እና የጽናት ዓመታት በሚል መሪቃል በመሰባሰብ እና ይህን የድርጅቱን ስራዎች አስቀድሞ ይፋ በማድረግ ለአባላቱ ምስጋናዉን አቅርቧል። ይህ በዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች በጋራ የሚከበረዉ የምስጋና በዓል ባህልን፤ ወደ ኢትዮጵያ ብንወስደዉ ምን ይለናል? ወይስ እኛ ኢትዮጵያዉያን የራሳችን የምስጋና ቀናት አሉን? ስንል ለዶ/ር ዮሃንስ ዘለቀ  ጠይቀናቸዋል። 

ዶክተር ዮሃንስ ዘለቀ ሲመልሱ፤ «ኢሬቻ እኮ «ታንክስ ጊቪንግ» ነዉ በኢትዮጵያ። ግንቦት ልደታ እኮ የምስጋና ቀን ነዉ በኢትዮጵያ። «ታንክስ ጊቪንግ» እኮ በየሳምንቱ ማህበር፤ ሰንበቴ እያልን የምንሰባሰብበት የምንጠጣበት የምንበላበት የምንፀልበት ምስጋና የምናቀርብበት እኮ መድረካችን ነዉ። እነዚህ ባህሎቻችን እኮ በሙሉ፤ ከአሜሪካዉ «ታንክስ ጊቪንግ»  በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩ ናቸዉ። የማንለዉጣቸዉ ባህሎቻችን ናቸዉ። ይህ ከ 30 እና 40 ዓመት ወዲህ የመጣዉ ፖለቲከኛ ግን፤ ይህ የክርስትያን ነዉ፤ ይህ የኢስላም ነዉ፤ ይህ የኦሮሞ ነዉ፤ ይህ የአማራ ነዉ ፤ ይህ የከንባታ ነዉ እያለ፤ የነበረንን ባህል እና የምስጋና ቀናት ሁሉ አጠፋብን።  አገራችን ኢትዮጵያ፤ እጆችዋን  ወደ አምላክዋ ትዘረጋለች የሚል ታሪክ ነዉ ያላት። ከማንኛዉም የዓለም ሃገራት የምስጋና ቀን ያለት የመጀመርያዋ ሃገር ኢትዮጵያ ናት።» 

ዘጠኝ የኢትዮጵያ የግብረ- ሰናይ ተቋማት የጥምረት እርዳታ በምስጋና በዓል-አትላንታ ምስል Thewodros Tadesse/DW

በሰሜን አሜሪካ በአትላንታ እንደሚገኘዉ እንደ « ተስፋ ለኢትዮጵያ» ድርጅት ሁሉ በርካታ ኢትዮጽያዉያን ከዳክዬዉ ጥብስ ጎን ለጎን፤ የምስጋናንን ቀን ቡና አፍልተዉ፤ ዳቦ ደፍተዉ፤ የቻሉም ጠላ ጠምቀዉ፤ ጠጅ ጥለዉ፤ ቁርጥ ክትፎዉን አስከትለዉ፤ እንደባህላቸዉ እንኳን አደረሰህ  አደረሽ ተባብለዋል፤ መገናኛ መድረክም አዘጋጅተዋል። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝዉ እና ዘንድሮ 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረዉ፤ የኢትዮጽያ ህብረተሰብ አገልግሎት የልማት ማህበር «ECDC» ላለፉት በርካታ ዓመታት የዩናይትድ ስቴትሱን ብሔራዊ የምስጋና በዓል የሚያከብረዉ በዋሽንግተን እና አካባቢዉ ቤት አልባ ኢትዮጽያዉያን እና ሌሎች አፍሪቃዉያንን ቤት አልባ ዜጎችን በማሰባሰብ ነዉ።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW